በየሦስት ዓመቱ በሕዝብ ጤና አጠባበቅ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው የዓለም ጤና አጠባበቅ ማኅበራት ፌዴሬሽን 13ኛውን ጉባዔውን አዲስ አበባ እንድታስተናግድ ተወስኖ ዝግጅቱ እየተካሄደ ነው፡፡
ከሚያዝያ 23 እስከ 27 በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ከተለያዩ የዓለም አካባቢዎች የሚገቡ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡
የስብሰባውን ዝግጅት በጋራ የሚመሩት የዓለም የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኡሩሻ ላሣር እና የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተዋበች ቢሻው ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ ታንዛኒያ ውስጥ ከመደረጉ በስተቀር ሌሎቹን አሥራ አንዱንም ጉባዔዎቹን በበለፀጉ ሃገሮች ውስጥ ያደረገው የዓለሙ የጤና ማኅበር የዘንድሮው ጉባዔው አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ የተወሰነው ከሌሎች ሃገሮች ጋር ከተደረገ ውድድር በኋላ መሆኑን ዶ/ር ተዋበች ቢሻው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ፕሬዚደንቷን ያነጋገረው እስክንድር ፍሬው ያሰናዳውን ዘገባ ያዳምጡ።