ለመብት ከበሬታ ያለማወላወል ጠንክረው የሰሩ አስር ሴቶች ዓመታዊውን International Women Of Courage የተባለውን ሽልማት በስቴት ዲፓርትመንት ተቀበሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ሀገራቸው በመካከለኛው ምስራቅ የዲሞክራሲን ጎዳና በተያያዙ ሀገሮች የሴቶች አቅም ግንባታ ላይ የጸና ኣቋም እንደሚኖራት አረጋገጡ። ሚንስትር ክሊንተን ይህን ያረጋገጡት በትናንትናው አንድ መቶኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዚህ በዋሽንግተን በስቴት ዲፓርትመንት ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ ሀገሮች ለተመረጡ አስር ሴቶች INTERNATIONAL WOMEN OF COURAGE የተባለውን ዓለም አቀፍ ሽልማት ባበረከቱበት ስነ ስርዓት ላይ ነው.
ከተሸላሚዎቹ መካከል የኪርጊዝ ፕሬዚደንት ሮዛ ኦቱንባዬቫ እና ካሜሩናዊትዋ ጋዜጠኛ ሄንሪየት ኤክዌ ኡቦንጎ ይገኙባቸዋል።
በሽልማቱ ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ባለቤት ሚሼል ኦባማ በክብር ዕንግድነት ተገኝተዋል።