በየመኑ ፕሬዝዳንት አሊ አብዱላ ሳልህ ታማኝ ኃይሎችና በተቃዋሚ ወገኖች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል።
በመዲናይቱ ሰንዓ በዛሬው ዕለት በተካሄደ ውጊያም የተቃዋሚዎች ይዞታ የሆነ የቴሌቭዥን ጣቢያ መደርመሱ ተዘግዟል። ብሎም የሰንዓው ብጥብጥ ወደ ጎረቤት ከተሞችም እየተዛመተ መሆኑን ዘገባዎች እያመለከቱ ነው።
ድንገቱ ቀድሞውንም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ በዚያች አገር ለሚኖሩ ስደተኞች ደግሞ ጨርሶ መያዣው ወደጠፋበት አዝማሚያ እያመራ ነው።
የኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ውሎና አዳር በሁለት ወጣት ሴቶች አጋጣሚና ዕጣ ውስጥ ይመለከታሉ።
ለዝርዝሩ ቀጣዩን ዘገባ ያድምጡ።