በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክርክር፥ በኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ኅግና የመገናኛ ብዙኃን ይዞታ


«መንግስትን በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀስ በአሸባሪነት ተወንጅሎ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተረጋግጧል። የሆነውም ይሄው ነው።» አቶ መኮንን ካሳ። «ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ አቶ መለስ ናቸው።» አቶ ግዛው ለገሰ።

የጸረ-ሽብር ህግና የመገናኛ ብዙኃን የምሽቱ እሰጥ አገባ ትኩረት የሚያደርግበት ርዕስ ነው።

ኅጉ ረቂቅ ሳለ የሁለት ወገኑን የተቃርኖ ዕይታዎችን ያንጸባረቁት ተሳታፊዎች ናቸው፥ ዛሬ ኅጉ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ባሉት ሁኔታዎችም ላይ እንዲከራከሩ የተጋበዙት።

አቶ መኮንን ካሳ ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ከሲያትል ከተማ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ከዋሽንግተን ዲሲ የመንግስቱን ፖሊሲ በመቃወም ይከራከራሉ።

ተከራካሪዎቹ በኢትዮጵያ የንግግርና የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት መጪ ዕጣ ዙሪያ የሰነዘሩት አስተያየት በሦሥተኛው ክፍል ተካቷል።

የክርክሩን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

ሁለተኛውን ክፍል ለመስማት ከዚህ በታች ያለውን ይጫኑ፤

በመጪው የኢትዮጵያ የንግግር ነጻነት ዕጣ ላያ ያተኮረውን የተከራካሪዎቹን አስተያየት ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG