በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉራ ፈርዳ ተፈናቃዮቹ አሁንም ስጋት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ


ቢፍቱ ከተማ
ቢፍቱ ከተማ

ከደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት ደርሶባቸው ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የሚናገሩ በትምሕርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች፤ ከጥቃት ነፃ ስለመሆናቸው ዋስትና እንደሌላቸው ገለፁ።

በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ቁጥርም 41 እንጂ መንግሥት እንዳለው 31 አለመሆናቸውን ተናግረዋል። የተፈናቃዮቹም ቁጥር 7 ሺሕ እንደሚደርስ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ ለደረሰው ጥቃት ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን 54 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፆ፤ የተገደሉ ሰዎች ደግሞ 31 መሆናቸው በሁለም የፀጥታ አካላት የተጣራ መሆኑን አስታውቋል።

“ታጥቀው አከባቢውን ያተራምሱ ነበሩ» የተባሉ ሁለት ሽፍቶችም መገደላቸውን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የጉራ ፈርዳ ተፈናቃዮቹ አሁንም ስጋት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:36 0:00


XS
SM
MD
LG