በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ ክልል የቤተሰብ አባሎቻቸው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አቤቱታ


Map locating Amhara and Oromiya regions where protests occurred in Ethiopia.
Map locating Amhara and Oromiya regions where protests occurred in Ethiopia.

በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡና ሰዮ ኖሌ ወረዳዎች ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሸማቂዎችን በመደገፍ ተጠርጥረው የተያዙ ከአንድ መቶ አርባ በላይ ሰዎች ለወራት በፖሊስ ሳይጠየቁ ወይም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እንደሚገኙ የቤተሰቦቻቸው አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

"በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ የለም" ያሉት የኦሮምያ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ከተያዙት አብዛኛዎቹ የኦነግ ሸኔ አባላት ስለሆኑ ወይም ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት ስላላቸው ነው" ብለው ዳኛ ፊት ያልቀረቡት ፍርድ ቤቶች ዝግ በመሆናቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል “ሃያ የሚሆኑ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ የምሥራቅ ወለጋ የዞንና የወረዳዎች አመራር አባላት ከታሰሩ ከአንድ ወር በላይ ሆኗቸዋል” ሲሉ የፓርቲው አስተባባሪዎች አቤቱታ አሰምተዋል።

በነቀምቴና ምሥራቅ ወለጋ 4 ወረዳዎች ውስጥ የታሰሩት እነዚህ ግለሰቦች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውም ተገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኦሮምያ ክልል የቤተሰብ አባሎቻቸው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:58 0:00


XS
SM
MD
LG