ዋሺንግተን ዲሲ —
በትግራይ ክልል በሰፊው የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ በመቀሌ ከተማ ቅዳሜ ዕለት ድብደባና ዝርፊያ ተካሄደባቸው።
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የተቃዋሚ ፓርቲ፣ ጥቃቱ የተለመደ የወንጀል ድርጊት ሳይሆን ባለፉት ወራት ውስጥ አራት የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎችን ህይወት ያጠፋ ተደጋጋሚ ጥቃት አካል ነው ብሏል።
የትግራይ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ገብረሚካዔል መለስ በክልሉ በፖለቲካ አመለካከቱ ጥቃት የደረሰበት ወይንም የሚደርስበት ሰው የለም ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ