በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሚሶም ቅነሳ እየተጀመረ ነው


አሚሶም በሚል ምኅፃር የሚጠራው የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሶማሊያ መውጣት እንደሚጀምር እዚያው የሚገኙት የተልዕኮው አዛዥ አስታወቁ።

ለአሚሶም ጦር ያዋጡት ዩጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ጂቡቲ ናቸው።

የአፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ ግዳጅ አዛዥ ፍራንሲስኮ ማዴይራ ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሶማሊያ ውስጥ ተሠማርተው የሚገኙ አንድ ሺህ ወታደሮች በመጭው የአውሮፓ ወር መውጣት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

“የወታደሮች እንቅስቃሴ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ተጀምሯል፤ በመጭዎቹ ሣምንታትም ይቀጥላል። ይህ ቅነሳውን ለመጀመር እየተካሄደ ያለ የሽግሽግ ሂደት ሲሆን የሃገሪቱን የደኅንነት ጥበቃ ኃላፊነቶች ለሶማሊያ ብሄራዊ የፀጥታ ኃይሎች የማስተላለፍ ሥራም አብሮ ይጀመራል” ብለዋል።

ለአሚሶም ጦር ያዋጡት አምስት ሃገሮች ሠራዊቶቻቸውን ላለፉት አሥር ዓመታት ካሠፈሩባት ሶማሊያ እንደሚያስወጡ ከአንድ ዓመት ለዘለቀ ጊዜ ሲያሳወቁ የቆዩ ሲሆን አሁንም የቅነሳው እንቅስቃሴ የሚካሄደው የሶማሊያን ሕዝብ ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥል በማይችል ሁኔታ እንደሚሆን የአፍሪካ ኅብረቱ ኃይል አዛዥ አመልክተዋል።

የአሚሶምን ቁጥር የመቀነሱ ዜና የተነገረው ዓለምአቀፉ ኃይል አልሻባብን ከታችኛው ሸበሌ ክልል ለመጠራረግና የመገናኛ መሥመሮቹን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመቻ እንደሚጀምር ባወጀ ማግስት ሲሆን የአፍሪካ ኅብረት ኃይል ከዚያ የሚወጣው የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ለመረከብ ዝግጁ መሆኑን ሲያረግጥ ብቻ እንደሆነ ማዴይራ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ግን ‘ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደሮቿን ሰሞኑን ወደ ሶማሊያ አስገብታለች’ ተብሎ የተነገረውን ማዴይራ አስተባብለው እንቅስቃሴው መደበኛ የሆነ የጦር ቅይይር ወይም ዝውውር እንደነበረ አመልክተዋል።

“እነዚህን እንቅስቃሴዎች ታያላችሁ፤ እንቅስቃሴዎቹ ደግሞ ኢትዮጵያንም ይጨምራሉ። ከዩጋንዳ የሚመጡት ወታደሮች በአየር ይገባሉ፤ ኢትዮጵያዊያኑ ድንበር አቋርጠው ይገባሉ። ምክንያቱም በቀጥታ ነድተው ሊገቡ ይችላሉና። ሌላ ዓላማ ያላቸው ሰዎች ኢትዮጵያ ጦሯን ሶማሊያ ውስጥ እያከማቸች ነው እያሉ ያወራሉ” ብለዋል የአሚሶሙ አዛዥ።

358 ሰው የተገደለበትና የ54 ሰው ደብዛ መጥፋቱ የሚነገርበት ጥቅምት 4 ሞቃዲሾ ላይ ከተጣለው የፈንጂ አደጋ ማግስት አልሻባብ ላይ ይከፈታል ለተባለው ጥቃት ድጋፍ ለመፈለግ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት በቅርቡ ወደ ዩጋንዳ፣ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ሄደው ነበር።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአሚሶም ቅነሳ እየተጀመረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG