በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንጎላ በሰብአዊ መብት አያያዝዋ ላይ ጫና በርትቶባታል


የአንጎላ ባንዴራ
የአንጎላ ባንዴራ

አንጎላ በሰብአዊ መብት አያያዝዋ ላይ ጫና እየበረታባት ነው። የአውሮፓ ምክር ቤት በቅርቡ አንጎላ ውስጥ በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ የተባሉ ተቃዋሚቆች በፍጥነት እንዲፈቱ ጠይቋል። በደቡባዊ አፍሪቃ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ አኒታ ፖል የላከችውን ዘገባ አዳነ ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

የአውሮፓ ምክር ቤት አንጎላ በተቃዋሚዎች ላይ የምታሳየውን አያያዝ አውግዞ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችና ለሰብአዊ መብት የሚታገሉ ሰዎች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል። በርካታ የሰብአዊ መብትና ህግ ነክ ጅርጅቶችም፣ የምክር ቤቱን ውሳኔ ደግፈዋል።

የአነጎላ መንግስት ከቅርብ ወራት ወዲህ ቢያንስ 15 ተቃዋሚዎችን አስሯል። ከነሱም መካከል ተቃውሞን በማስተባበር ተግባር የተከሰሱት Jose Marcose Mavungo ናቸው። ክሱ ሀይል ተጠቅሚነት አቀጣጥለዋል የሚል ሲሆን፣ በፍርድ ቤት ሂደት የቀረበ ማስረጃ አልነብረም። ባለፈው መስከረም ወር ተከሰው የስድስት አመታት እስራት ተበይኖባቸዋል።

Muluka Miti-Drummond የደቡባዊ አድሪቃ የክስ ሂደት ማዕከል ስራ-አስኪያጅ ናቸው። መዕከሉ የአውሮፓ ምክር ቤት የወሰደውን ውሳኔ ከደገፉት 15 ድርጅቶች አንዱ ነው። የአንጎላ መንግስት ይህን የሚያደርገው በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል ነው ብለዋል።

“SALC ን የመሳሰሉት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዲህ አይነቱን ድርጊት በመናገር ነጻነት ላይ የሚፈጸም ፍትህ የጎደለው ገደብ አድርገን እናያዋለን የፖለቲካ አላ አለው ብለንም እናምናለን።”

አንጎላ ያሉት ተቃውሚዎች ሀገሪቱ በነዳጅ ዘይት ምርት ከአፍሪቃ ሁለተኛዋ ሆና ሳለ በሀገሪቱ ያለው የድህነትት ሁኔታና የእኩልነት ጉድለት እንደሚያሳዝናቸው ተቃዋሚዎቹ ይናገራሉ። እአአ ከ 1979 አም አንስቶ በአንድ ሰው የምትገዛ ሀገር መሆነዋን ያስገነዘቡት ተቃዋሚዎች የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ መብት እንደሌለ ይናገራሉ።

በአንጎላ የፍርድ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብት ክፍል የአውሮፓውን ምክር ቤት ውሳኔ “የስም ማጥፋት ወሬ ነው” ብለውታል።

Miti-Drummond በበኩላቸው የአውሮፓው ምክር ቤት ውሳኔ አንጎላ ጥያቄውን ባትቀበል ምን እንደሚያደርግ አይገልጽም ብለዋል።

ዝርዝሩን ለመስማት የተያያዛውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

አንጎላ በሰብአዊ መብት አያያዝዋ ላይ ጫና በርትቶባታል /ርዝመት - 2ደ08ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG