በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንገላ መርከል የናንሰን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ


አንገላ መርከል የናንሰን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

አንገላ መርከል የናንሰን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

የቀድሞ የጀርመን ቻንስለር አንገላ መርከል ከሦሪያ ጥቃትና ግድያን ሸሽተው ለወጡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መጠጊያ በመፍጠራቸው ከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ሽልማት የሆነውን፣ የናንሰንን ሽልማት አሸንፈዋል፡፡

አንገላ መርከል የሦሪያው ጦርነት ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት እአአ በ2015 እና 2016 በነበረው ጊዜ ሌሎች አገሮች ፊታቸውን ያዞሩባቸውን የሦሪያ ስደተኞች በደስታ ተቀብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሥደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ መርከል ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ስደተኞች ህይወት በማትረፍና መልሰው እንዲቋቋሙ ለመርዳት የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ትልቅ የሞራል ልዕልና አሳይተዋል ሲሉ በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ወቅት ተናግረዋል፡፡

መርከል የስደተኞችን ችግር ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ ረድተዋል ያሉት የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ማቲው ሶልት ማርሽ ፈታኝ የሆኑ ሁኔታዎች ሲገጥሙ ፖለቲከኞች ኃላፊነትን ወደሌሎች ከማሸጋገር ይልቅ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ሥራ ሲሰሩ ምን ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ መርከል አሳይተዋል ብለዋል፡፡

ሶላት ማርሽ አያይዘው፣

“እንዲሁም ጦርነትን፣ ግድያንና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመሸሽ የተገደዱ ሰዎችን በመጠበቅና በጀርመን እነሱን በመቀበል በአዲሱ ቤታቸው በትምህርት፣ በሥልጠና መርኅ ግብሮች፣ በሥራ ቅጥርና ሥምሪት የተደረገውን የጋራ ጥረት በማገዝ በኩል የቀድሞዋ ቻንሰለር አስተዋፆዖ ከፍተኛ ነበር” ብለዋል፡፡

ሽልማቱ የተሰየመው በተመራማሪነትና እና በሰብዓዊነት በታወቀው ፍሪድጆፍ ናንሰን ስም ሲሆን ስደተኞችን ከመጠበቅ ጥሪ በላይ ርቀው በመሄድ ለግለሰቦች፣ ለቡድኖች ወይም ለድርጅቶች የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡

ተሸላሚዎችን የሚመርጠው ኮሚቴም ከሌሎች አራት የዓለም አካባቢዎች አሸናፊዎችን የመረጠ ሲሆን፡፡ ተሸላሚዎቹ በሙሉ በምዕራብ አፍሪካ ሞሪታኒያ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ቡድን አባላት የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ናቸው፡፡

እንዲሁም በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ አካባቢ በኮስታሪካ የስደተኞች ድጋፍ የሚሰጡ የካካዎ የህብረት ሥራ ማኅበር አባላት፣ በእስያ በፓስፊክ አካባቢ የማይናማር የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚረዱ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ለያዚዲ ልጃገረዶችና ሴቶች የአካላዊ እና የሥነልቦናዊ እንክብካቤ የሚያደሩት ኢራቃዊ የማህፀን ሀኪም ይገኙበታል፡፡

የናንሰን ሽልማት ለቀድሞዋ ቻንስለር መርከል እና ለአራት የክልል አሸናፊዎች መስከረም 30 በጄኔቭ በሚደረገ ሥነ ሥርዓት እንደሚሰጥ ተነገሯል፡፡

የገንዘብ ሽልማት በተካተተበት በዚሁ ሽልማት ለመርከል 150ሺ ዶላር የሚሰጥ ሲሆን ሌሎች የየአካባቢው አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 50ሺ ዶላር እንደሚበረከት ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG