ከየመን ሰንዓ ዓየር ማረፊያ ተወስደው ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ እስር ቤት የቆዩትና ከትናንት በስቲያ ከእስር የተለቀቁት የአርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋራ ቤተመንግሥት ተገናኝተው መነጋገራቸውና ሁለቱ ተጨባብጠው የሚያሳየ ፎቶ ግራፋቸው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በይፋ ከወጣ በኋላ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ በደቂቃዎች ውስጥ በብዙ ሰዎች ገጽ ላይ የተዘዋወረ ነበር።
በኢትዮጵያ ሕገመንግሥታዊነት እንዲከበር ጥያቄን የሚያነሱና በተለያየ ጊዜ ታስረው የተፈቱ ሦስት ወጣት የመብት አራማጆችን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስለሚያከናውኑት ተግባራት ያላቸውን አስተያየት ጠይቄያቸዋለሁ። በተለይ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተሰጠውን ውሳኔና በቤተመንግስቱ ውስጥ ያደረጉት ውይይትና የታየው የአብሮነት ፎቶ ግራፍ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ የሚኖረውን ትርጉም አስተያየት ሰጥተውበታል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ