የወታደሮቹን ድርጊትና በመጨረሻውም ሂደቱ የተቋጨበትን ሁኔታ አስመልክቶ በጠቅላይ ሚንስትሩ በራሳቸውና በሌሎች ባለ ሥልጣናት የተሰጡ አስተያቶች፣ ድርጊቱ ከወታደራዊ ሥርዓት አጠባበቅ አንጻር የሚታይበትንና ብሎም ሁኔታው የፈጠረውን አንድምታ እና እንዲሁም ምንነት የሚገመግም ቃለ ምልልስ ነው።
ለትንታኔው በሲቪል አስተዳደር እና በወታደራዊ ሞያ በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ባለ ሞያ ጋብዘናል።ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ የኤርትራ ዋና አስተዳዳሪና የእርዳታ ማስተባባሪያና ማቋቋሚያ ኮምሽን ኮምሽነር በመሆን በሲቪል አስተዳደር ውስጥ ያገለገሉና በወታደራዊው ጎራ መጀመሪያ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የጦር አካዳሚ የጦር መኮንነት ኮርስ የተከታተሉ፣ ቀጥሎም በዓየር ወለድና የኮማንዶ ትምሕርቶች ልዩ ሥልጠና የወሰዱ፤ እንዲሁም በእሥራኤል የልዩ ኃይል (Special force) ሥልጠና በዩናይትድስ ስቴትስ ፎርት ቤኒንግ ከፍተኛ የእግረኛ ጦር ሥልጠና እንዲሁም ፎርት ቶማስ ኬንታኪ የውትድርና አስተዳደር ሞያ የሰለጠኑ ናቸው።
ከሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ጋር ያካሄድነውን ቃለ ምልልስ ተከትሎም ቀደም ብሎ በተነሱት ጥያቄዎች ዙሪያ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋን አነጋግረናል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ