በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሀገሪቱ በአስቸኳይ ሕጋዊ ተቋማትን ልትገነባ ይገባል” - ባለሞያዎች


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የሰጡት መግለጫ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የሰጡት መግለጫ

በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችንና ሞቶችን ለማስቀረት ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማስገባትና ፍትሐዊና ሕጋዊ ተቋማትን መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ያነጋገርናቸው ባለሞያዎች ገለፁ።

ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ንግግር ያደረጉሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፤ በሚያሳፍር ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች አሁንም እየሞቱ፤ በተጨማሪም ሰዎች በሰላም ወጥተው መግባት እንዳልቻሉ ገልፀው “ይህን ድርጊት ለሚፈፅሙ አካላት የመጨረሻ የሰላም ጥሪዬን አቀርባለው” ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ ባለሞያዎች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እስካሁን ያከናወኗቸውን መልካም ነገሮች የሚያጠናክር፣ ሀገሪቱን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ የሚመልስና የወደፊቱን አቅጣጫ አመላካች የሆነ ጥርጊያ መንገድ ሊያሳዩን ይገባል ብለዋል።

ጽዮን ግርማ የታሪክ መምሕሩን አቶ አበባው አያሌው፣ የሕግ ባለሞያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ አቶ ጃዋር መሐመድን ከዩናይትድ ስቴስት አነጋግራ በተከታዩ ዘገባ ይዛቸዋለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

“ሀገሪቱ በአስቸኳይ ሕጋዊ ተቋማትን ልትገነባ ይገባል” - ባለሞያዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG