በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአቶ በረከት ስምኦን ጉዳይ ..


አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል
አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል

"እፎይታ ተሰምቶኛል። እኝህ ሰው በኢትዮጵያ በተፈጸመው የመብት ረገጣ እጅግ የከፋ የመብት ጥሰትና የተዛባ መረጃ በማሠራጨት ሚና ነበራቸው ብዬ ስለማምን በኃላፊነት በመጠየቃቸው ትልቅ እፎይታ ነው የተሰማኝ።" አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል።

በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት ቀድሞው የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሚንስትር የአቶ በረከት ስምኦን እስር ዜና አሁንም እያነገገረ ነው።

አቶ በረከት በገዥው ፓርቲ ውስጥ የነበራቸውንና ለረዥም ዓመታት የዘለቀ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚናና የመንግሥት ሥልጣን ተንተርሶ የተለየ ትኩረት የሳበው እስራቸው፤ ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ አስተያየትችን ጋብዟል።

ከዚህ ቀደም በትዊተር አማካኝነት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች “አቶ በረከት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የሚል አስተያየት የሰነዘሩት የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ ሚስ አና ጎሜሽ የቀድሞው የኢሕአዴግ ባለ ሥልጣን እስር ዜና እንደተሰማ እርምጃውን በማወደስ ፈጥነው አስተያየታቸውን ካሰፈሩት ውስጥ ናቸው።

አቶ በረከት ስሞኦን
አቶ በረከት ስሞኦን

ሚስ አና ጎሜሽ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲያ ጉዳዮች ዙሪያ ጠንከር ያሉ ትችቶችን በማቅረብም ይታወቃሉ። ይህንኑ አስተያየታቸውን መነሻ በማድረግ ከሚስ ጎሜሽ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ዝርዝሩን ይዟል።

“የተከሰሱበትን ጭብጥ ሙሉ በሙሉ ባላውቅም .. በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በደረሰው በደል፣ በበኩላቸው በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ይሆናሉ፤ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።” የሚሉት ሚስ ጎሜሽ - የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚያ ቀደም ታይቶ በማያውቅ ደረጃ ወጥቶ ድምጹን በሰጠበት፣ የአውሮፓ ሕብረትን በመወከል በታዛቢነት በተሳተፉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ያዩትን ዋቢ አድርገው፤ ከአቶ በረከት ጋር በቀጥታ የተገናኙባቸውን ጊዜያት ያነሳሉ።

በኢትዮጵያ በመጣው “እጅግ አሰደናቂ” ባሉት ለውጥ .. ከሀገራቸው ውጭ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር እንዲገቡ መደረጋቸው፣ የሚያምኑትን በግልጽ መናገር መቻላቸው “አሳድሮብኛል” ያሉትን ትልቅ ተሥፋም ሚስ ጎሜሽ ገልጠዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአቶ በረከት ስምኦን ጉዳይ ..
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG