በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአምነስቲ ተመራማሪ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ተፈጽመዋል ስለተባሉት ጥሰቶች የሰጡን ማብራሪያ


ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል “ሕግ ከማስከበሩ ባሻገር” በሚል ባወጣው ሰፋ ያለ የ50 ገፅ ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የከፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ዘርዝሯል።

ግድያ፣ ጅምላ እስር፣ የማሰቃየት ተግባራት እና በእስር ቤቶች ውስጥ ተፈፅመዋል የተባሉ ሁለት ፆታዊ ጥቃቶች ማሳያዎች በሪፖርቱ ውስጥ ተካተዋል። ድርጅቱ በመንግሥት በኩል ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አኳያ መሻሻሎች መኖራችውን አስታውሶ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ኃይሎች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶች አሳሳቢ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ጽዮን ግርማ የድርጅቱን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አጥኒ አቶ ፍሰኃ ተክሌን አነጋግራ ያሰናዳችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአምነስቲ ተመራማሪ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ተፈጽመዋል ስለተባሉት ጥሰቶች የሰጡን ማብራሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:39 0:00


XS
SM
MD
LG