በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት በማስነሳት የተጠረጠሩ ታሰሩ


አቶ ምግባሩ ከበደ
አቶ ምግባሩ ከበደ

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት አስነስተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 224 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋሉት በምዕራብና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በኦሮሞ ብሄረስብና በሰሜን ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ መሆናቸውን ዐቃቤ ሕጉ ጨምሮ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ እየታዩ ያለውን የፀጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የክልሉ መንግሥት አዲስ የፀጥታ ኃይል ሥምሪት ማዋቀሩን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት በማስነሳት የተጠረጠሩ ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG