በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ከጎርፍና ከመሬት መንሸራተት ጋር በተያያዘ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 37 ደረሰ


ጎርፍና የመሬት መንሸራተት 39 ሰዎችን ገድለዋል
ጎርፍና የመሬት መንሸራተት 39 ሰዎችን ገድለዋል

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ፣ በግዳን፣ ዋድላና በራያና ቆቦ ወርዳዎች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በደቡብ ወሎና በተለያዩ አካባቢዎች ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በሰው ሕይህወት፣ በከብቶችና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

አከታትሎ በመጣል ላይ ያለው ዝናብ በአምስት ወረዳዎች 37 ሰዎችን ሲገድል ከ6ሽህ በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የአማራ ክልል ባለስልጣን አስታወቁ።

የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ታምራት ደጀኔ ለቪኦኤ ሲናገሩ፡-“አጠቃላይ አደጋው የደረሰው አንደኛ በጎርፍ ጋር በተያያዘ ነው፤ ሁለተኛ ተራራ መንሸራተት ጋር ተያይዞ እዚያ አካባቢ የሰፈረው ሰው ላይ የተናደበትና ህይወቱን ያጣበት… ሁኔታ ነው” ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዜና ምንጭ በጎርፍ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን ሰዎች ቁጥር ከ8ሽህ በላይ አድርሶታል።

የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ ሰራተኞች ለተጎጂዎች የጊዚያዊ የምግብ፣ የመጠለያና የመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያዎችን እያከፋፈሉ እንደሆነ አቶ ታምራት ገልጸዋል።

“በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት አዳራሾች፣ ትምህርት ቤቶች፣ አንዲሁም ድንኳን በማቅረብ ሰው እንዲጠለል ተደርጓል።”

በአንዳንድ ለመድረስ ያልተቻለባቸው አካባቢዎች ግን የእርዳታ አቅርቦት እስካሁን አልደረሰም። በአማራ ክልል ይሄን መሰል ከባድ ዝናብና ጎርፍ ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም።

XS
SM
MD
LG