ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉት ነዋሪዎች የመፈናቀላቸው ምክኒያት “ፍርሃት እንጂ የፀጥታ ችግር አይደለም” ሲሉ የዞኑ የሰዲ ጨንቃ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ።
በወረዳዋ በሕክምና ሥራ ላይ የሚተዳደሩ ነዋሪ በበኩላቸው፤ “የተፈናቃዮቹን ንብረት የነካ የለም አንዳንዶቹ ወኪል አድርገዋል የሌሎቹ ደግሞ በሀገር ሽማግሌ እየተጠበቀ ነው”ይላሉ።
ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ “የተደራጁ ኃይሎች ንብረት አቃጥለው፣ መሰረታዊ አገልግሎት እንዳናገኝ ከልክለው፣ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ ብለው ሲያባርሩን ነው የኖርንበትንና ንብረት ያፈራንበትን መንደር ጥለን የተሰደድነው።” ይላሉ።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት 1 ሺሕ 400 የሚጠጉ የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ ለክልሉ ብዙሃን መገናኛ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
የፌደራልና የክልል ቃል አቀባዮች ስልካቸውን ስለማያነሱ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ