በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና በኦሮሚያ ክልል አጎራባቾች ግጭት ተከሰተ


በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ግጭት መከሰቱን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እስከ ትናንት በዘለቀው ግጭት ለጊዜው ይፋ ባይሆንም ጉዳት መድረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ግጭቱ ዛሬ መረጋጋቱን መረጃዎች አመልክተው የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ውይይት ጀምረዋል፡፡

የጸጥታ ኃይሉም የአካባቢውን ሰላም ለማረጋጋት ስራዎችን እየሰራ ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ወኪል መስፍን አራጌ የዞኑን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቅሩ ሳሌ ን በስልክ አነጋግሯቸዋል፡፡ በችግሩ መንስኤ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ፡፡

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራና በኦሮሚያ ክልል አጎራባቾች ግጭት ተከሰተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:44 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG