በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላም ንግግሩ ቀጣይ ፈተናዎች


የሰላም ንግግሩ ቀጣይ ፈተናዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00

የትግራይ አማጽያን በኬንያ አስተናጋጅነት የሚደረግን ድርድር እንደሚቀበሉ ካሳወቁ በኋላ በኢትዮጵያው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑት ወገኖች ወደ ሰላም ንግግር እየተቃረቡ ይመስላል። የአማጽያኑ መግለጫ የወጣው ማክሰኞ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥታቸው ከትግራይ መሪዎች ጋር ለሚደረግ ድርድር ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህወሓት ጋር የሚደራደር ኮሚቴ መቋቋሙን ማሳወቃቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም የሰላም ንግግግር አይቀሬ መሆኑን አመላካች ነው።

ተንታኞች እና የምክር ቤት አባላት እንደሚሉት ግን፣ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ፣ ክህወሓት እና ከፌዴራል መንግሥት ውጪ ያሉ ተዋናዮችም በጠረጴዛው ዙሪያ መቀመጫ ሊሰጣቸው ይገባል።

የፓርላማ አባሉና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄው ደሳለኝ ጫኔ እንደሚሉት ድርድሩ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩትን የአማራ ክልልንና በሰሜን የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችውን ኤርትራን ማሳተፍ አለበት።

“በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩትን ሁሉንም ወገኖች የማያሳትፍ ድርድር መክሸፉ የማይቀር ነው። የፌዴራል መንግሥት የአማራንም ሆነ የኤርትራን ጥቅም ችላ የሚል ከሆነ ሁለቱ ወገኖች የየራሳቸውን ጥቅም ወደ ማስጠበቅ ይገባሉ። እንደሚመስለኝ ዐቢይ የአማራንና የኤርትራን ምክንያታዊ ስጋት ተረድቶ ወደ ድርድሩ ጠርጴዛ መጋበዝ አለበት” ብለዋል ደሳለኝ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ።

አክለውም መንግሥት እስከአሁን እንዲህ ዓይነቱን ዋስትና አልሰጠም ብለዋል።

ሰላማዊት ካሳ የፌዴራል ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴታ ናቸው። መንግሥት ያቋቋመው ኮሚቴ የድርድሩን “አጠቃላይ ሂደት ይመራል” ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

“መንግሥት ከዚህ በተጨማሪ ሀገራዊ መግባባትን ለማበረታታት፣ ሁሉንም የሚያካትትና ሰፋ ያለ መሰረት ያለው ህዝባዊ ውይይት ለማድረግ ብሄራዊ ኮሚሽን አቋቁሟል” ብለዋል ሰላማዊት።

በማከልም “ሰላምን ለማምጣት አብረን እንቆማለን። ፌዴራል መንግሥቱ የሰላም ድርድሩን የሚከታተል ኮሚቴ አቋቁሟል። ይህ ሂደትም ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን የሚያሳትፍ የሆናል” ብለዋል።

ለህወሓት ግን የድርድሩ ሸምጋዮች ማን ናቸው የሚለው ጥያቄ አንገብጋቢ የመስላል። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ “የአፍሪካ ህብረት መሪዎች የአማጺያኑን እምነት ማግኘት አለባቸው፥ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያላቸውን ቅረበት ሳናስተውል የቀረነው ጉዳይ አይደለም” ብለዋል።

“በዚህም መሰረት” ይላል መግለጫው በመቀጠል፣ “አሁን ባለውና ተደራዳሪ ወገኖቹ በተስማሙት ሥምምነት መሰረት በኬንያው መሪ አመቻችነት በናይሮቢ ለሚደርግ ድርድር ያለንን ጠንካራ ፍላጎት እንገልጻለን” ብሏል።

ተንታኙ ዊሊያም ዴቪድሰን ቤልጂየም መሰረቱን ካደረገው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ከሚባል የምርምር ተቋም ሲሆን እሱ እንደሚለው ከአካታችነትና ሌሎች የድርድር ሁኔታዎች ውጪ የሆኑ ችግሮችም መፈታት አለባቸው።

“ለሰላም እንቅፋት የሚሆኑ ሌሎች ያልተፈቱ ችግሮች አሉ። የመጀመሪያው በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መመለስ ነው። በተለይም የባንክ የስልክና የኤሌክትሪክ. . . . ከዛ ደግሞ ህውሃት እንደ ሽብርተኛ ቡድን የተሰየመበት ጉዳይ ነው. . . . ከሁሉ በላይ ግን የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ነው።”

የአማራው ወገን ምዕራብ ትርግራይን በጦርነቱ ወቅት ከህወሃት ነጥቆ በእጁ ካስገባ በኋላ መልሶ እንደማይሰጥ አስታውቋል። ህወሃት ደግሞ በበኩሉ ቦታው መመልስ እንዳለበት ያሳስባል።

ኢትዮጵያዊው ተንታኝ ኪራም ታደሰ እንደሚለው በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ድርቅ፣ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ችግሮች ሁለቱንም ወገኖች ወደ ሰላም እየገፋቸው ሳይሆን አይቀርም።

“በጦርነት እየተሳተፉ ያሉት ወገኖች ምርትና የኢኮኖሚ እንቃስቃሴ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ከሆነ አጠቃላይ ሁኔታው የዜሮ ድምር ውጤት ይሆናል።”

ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አህመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግርም የልማት እንቅስቃሴው በጦርነት ምክንያት ጋሬጣ ተደቅኖበታል።

XS
SM
MD
LG