በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያኑ ባህላዊ ማዕድ እና አብሮነት ታዛ - በሚልዋኪ


የኢትዮጵያውያኑ ባህላዊ ማዕድ እና አብሮነት ታዛ - በሚልዋኪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:44 0:00

የማዕከላዊ ዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ግዛት በኾነችው ዌስካንሰን፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ የሚያቀርቡ፣ የአገሪቱን ባህል እና ትውፊት የሚያንጸባርቁ ስፍራዎችን ማግኘት፣ ጊዜ ወስዶ በስፋት ማሠሥን ይጠይቃል። “ዓለም የኢትዮጵያ መንደር” የተባለው አንዱ ምግብ ቤት፣ በከተማዋ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጠንካራ የማኅበራዊ ትስስር ታዛ ኾኖ ያገለግላል፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ደግሞ፣ የኢትዮጵያን ምግብ እና ባህል መተዋወቂያና ማጣጣሚያ ስፍራ ኾኖ ስለ መቆየቱ ይነገርለታል።

የማዕከላዊ ዩናይትድ ስቴትስ ምዕራባዊ ግዛት በኾነችው ዌስካንሰን፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ የሚያቀርቡ፣ የአገሪቱን ባህል እና ትውፊት የሚያንጸባርቁ ስፍራዎችን ማግኘት፣ ጊዜ ወስዶ በስፋት ማሠሥን ይጠይቃል። ምክንያቱ ደግሞ፣ የግዛቷ ትልቅ ከተማ በኾነችው ሚልዋኪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች ቁጥር ሁለት ብቻ መኾናቸው ነው።

“ዓለም የኢትዮጵያ መንደር” የተባለው አንዱ ምግብ ቤት፣ በከተማዋ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጠንካራ የማኅበራዊ ትስስር ታዛ ኾኖ ያገለግላል፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ደግሞ፣ የኢትዮጵያን ምግብ እና ባህል መተዋወቂያና ማጣጣሚያ ስፍራ ኾኖ ስለ መቆየቱ ይነገርለታል።

ሰሞኑን ወደ ሚልዋኪ ለዘገባ ያቀናው ሀብታሙ ሥዩም ቀጣዩን አጭር ቅኝት አሰናድቷል።

XS
SM
MD
LG