በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት አሜሪካውያን በኮንጎ መፈንቅለ መንግሥት ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጣሪ ሆኑ


 የኮንጎ የጸጥታ ኃይሎች በጥበቃ ላይ
የኮንጎ የጸጥታ ኃይሎች በጥበቃ ላይ

በኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ቤተመንግሥት ላይ በተፈፀምው ጥቃት፣ የኮንጎ እና አሜሪካዊ ዜግነት ባላቸው ክርስቲያን ማላንጋ የተሰኙ ፖለቲከኛ የተመሩ ሦስት አሜሪካውያን መሳተፋቸው ተገለፀ።

በወርቅ ማዕድን እና ያገለገሉ መኪናዎች ንግድ ላይ የተሰማሩት ማላንጋ፣ ዩታህ በተሰኘው የአሜሪካ ግዛት የተወለደ ልጃቸውን በከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት እንዲሳተፍ ማሳመናቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በመፈንቅለ መንግስቱ ማላንጋን ጨምሮ ስድስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሦስቱን አሜሪካውያን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸውን የኮንጎ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል ሲልቬይን ኢኬንጄ ተናግረዋል። ማላንጋ እሁድ ጠዋት ከፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች ጋራ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውንም ቃል አቀባዩ አክለው ገልፀዋል።

ባለሥልጣናቱ፣ የ21 ዓመት ዕድሜ ያለው የማሊንጋ ልጅ ለሚማርበት ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት እግር ኳስ ከመጫወት፣ እንዴት በስፋት በአፍሪካ ትልቁ አገር የሆነችውን መሪ በሀይል ወደማውረድ እንደተሻገረ ለመረዳት እየሞከርን ነው ብለዋል።

እናቱ ብሪትኒ ሳውየር ለአሶሽየትድ ፕሬስ በላከችው የኢ-ሜይል "ልጄ ንፁህ ነው" ስትል ምላሽ የሰጠች ቢሆንም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም። ሰኞ እለት በፌስቡክ ገጿ ባጋራችው መልዕክት ግን "ይህ አባቱን የሚከተል ንፁህ ልጅ ነበር። በየቦታው በሚለጠፉ እና ወደ እኔ በሚላኩ ቪዲዮዎች ተሰላችቻለሁ" ብላለች።

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚዘዋወር አንድ ቪዲዮ ልጇ በደም ከተጨማለቀ እና ማንነቱ በግልጽ ከማይታይ አንድ ነጭ ሰው ጋራ ሁለቱም በአቧራ ተሸፍነው እና በኮንግ ወታደሮች ተከበው ያሳያል። እጆቹን ወላይ ያነሳው ማርሴን፣ ፊቱ ላይ ፍርሃት ይነበብበታል።

አባቱ ማሊንጋ እ.አ.አ በ1990 ከቤተሰቦቹ ጋራ በስደት ወደ አሜሪካ መምጣቱን እና የኮንጎ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ በመሆን ከዋሽንግተን እና ከቫቲካን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋራ መገናኘቱን በድረ-ገጹ ላይ ያሰፈረው ግለ-ታሪኩ ያሳያል።

ሁለተኛው በመፈንቅለ መንግስቱ ተሳትፏል የተባለው ግለሰብ ቤንጃሚን ሪዩበን ዛልማን-ፖሉን የተባለ ግለሰብ መሆኑን የኮንጎ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው የአሜሪካ ፓስፖርት ምስል የሚያሳይ ሲሆን ማላንጋ እ.አ.አ በ2022 ሞዛምቢክ ውስጥ ባቋቋመው የወርቅ ማዕድን ማውጫ ኩባንያ የንግድ ሽርክና እንደነበራቸው ተመልክቷል።

በኪንሻሳ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ እሁድ ዕለት በተፈፀመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ "የአሜሪካ ዜጎች ተሳትፈው ሊሆን እንደሚችል" እንደሚያውቅ እና “በእነዚህ የግፍ የወንጀል ድርጊቶች ላይ በሚደረገው ምርመራ ” ከባለሥልጣናት ጋራ እንደሚተባበር አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG