በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የፓርላማ አባል መኖሪያ ቤት በጥይት ተደበደበ


የኮንጎ ሪፐብሊካን የጥበቃ ኃይል እና ፖሊስ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በተካሄደበት አካባቢ ጥበቃ እያካሄዱ፤ ጎምቤ፣ ኪንሻሳ እአአ ግንቦት 19/2024
የኮንጎ ሪፐብሊካን የጥበቃ ኃይል እና ፖሊስ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በተካሄደበት አካባቢ ጥበቃ እያካሄዱ፤ ጎምቤ፣ ኪንሻሳ እአአ ግንቦት 19/2024

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እሁድ እለት የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የጸጥታ ኃይሎች አክሽፈዋል። ታጣቂዎች በጥቃቱ የከፍተኛ ባለስልጣናት መኖሪያ ቤት ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን፣ በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ የሚገኘውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ለአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

እሁድ ጠዋት ውደ 50 የሚጠቁ ታጣቂዎች ከአካባቢው ጋር የሚመሳሰል ቀለም ያለው ልብስ በመልበስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በመከላከያ ሚኒስትሩ እና የፓርላማው አፈጉባዔ ይሆናሉ ተብለው በሚጠበቁት ከፍተኛ ባለስልጣን መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአገሪቱ ጦር አመልክቷል።

አጥቂዎቹ ጥቃቱን የፈፀሙት በማዕከላዊ ኪንሻሳ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኦፊሴላዊ መኖሪያ እና ዋና የስራ ቦታ የሆነው 'ፓላሲስ ደ ላ ኔሽን' ጥሰው በመግባት ነው።

የፓርላማ አባል የሆኑት ቪታል ካሜሬ ቃል አቀባይ ሚቼል ሞቶ ሙሂማ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል በካሚሬ መኖሪያ ቤት በደረሰው ጥቃት ሁለት ጠባቂዎች እና አንድ ጥቃት አድራሽ መሞታቸውን ገልጸዋል።

"በቦታው ስንደርስ አካባቢው የጦር ሜዳ ይመስል ነበር" ያሉት ሙሂማ፣ በየቦታው የወደቁ አስክሬኖች እና ቁስለኞች ይታዩ እንደነበር እና ፖሊሶች ካሜሬን ከጥቃቱ ማዳን መቻላቸውን ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG