በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችና ቤተሰቦቻቸው ዛሬ ሞስኮ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተነስተዋል። ሩስያ ጥንድ ሥለላ ያካሄዱ የነበሩ ሩስያዊ ሠላይን መርዛለች በሚል ክስ በአሜሪካና በሩስያ መካከል በተደርገው የዲፕሎማቶች መበረር እርምጃ ምክንያት ነው አሜሪካውያኑ ዲፕሎማቶቹ ከሩስያ የተነሱት።
ሩስያ ዲሎማቶቹ ከግዛትዋ እንዲወጡ የመደበችው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ሲሆን ሦስት አውቶብሶች ከአሜሪካ ኤምባሲ ወጥተው ወደ አይሮፕላን ማረፍያ ሲያመሩ መታየታችው ተዘግቧል።
ሰርገይ ስክሪፓልና ሴት ልጃቸው ከአንድ ወር በፊት ከተመረዙ ወዲህ በምላሹ የተለየዩ ሀገሮች ዲፕሎማቶችን የማባረር እርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይተዋል። አባትና ልጅ የተመረዙት በሶቭየት ኅብረት በተሰራ በወታደራዊ ደርጃ በሚታይ የነርቭ ኤጀንት ነው ትላለች ብሪታንያ።
ጥንድ ሥለላ ሲያካሄዱ ቆይተው በመጨረሻ ወደ ብሪታንይ የከዱት ስክሪፓልና ልጃቸው ሳልስበሪ በተባለቸው የለንደን ከተማ መናፈሻ ቦታ ላይ ነበር ተዘርረው የተገኙት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ