በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“መከላከያ በአምቦ 10 ሰው ገደለ” - የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ


ከ15 ሰው በላይ ቆስሏል ብለዋል። የሰራዊቱ አባላት እርምጃን ተከትሎ ሰልፈኞች በቁጣ የጭነት መኪናዎችን ማቃጠላቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ሕገ ወጥ ስኳር እየተዘዋወረ ነው በሚል በአምቦ ከተማ ዋና መንገድ ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተኩስ በመክፈት 10 ሰዎችን መግደላቸውን የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። በተጨማሪም ከ15 ሰው በላይ ቆስሏል ብለዋል። የሰራዊቱ አባላት እርምጃን ተከትሎ ሰልፈኞች በቁጣ የጭነት መኪናዎችን ማቃጠላቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አሁን ከተማዋ መሳሪያ በደገኑ መኪኖችና በታጠቁ ሰዎች ተሞልታለች ብለዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በዛሬውዕለት በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ “በእጅጉ የሚረብሽ ሁከትና ግድያዎች በአምቦ ከተማ ዛሬ መከሰታቸውን በዘገባዎች ሰምተናል። በኢትዮጵያ ዜጎች በሰላምና በፍጹም ነጻነት ሐሳባቸውን እንዲገልጹ ማበረታታት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል እንደሚፈጥር ልናሰምርበት እንወዳለን።” ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

“መከላከያ በአምቦ 10 ሰው ገደለ” - የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG