በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቲቦር ናዥ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዞ ማጠቃለያ


Tibor NAgy
Tibor NAgy

“ኢትዮጵያ በውጭው እንዲሁም ‘አንዳንድ’ - ባሏቸው - የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ስለከፈተችው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እያራመዱት ስላሉት መንገድ ምሥጋና ይግባውና...” ሲሉ ነው አምባሳደሩ የመክፈቻ መግለጫቸውን የጀመሩት።

ዩናይትድ ስቴትስ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ባሉ ለውጦች እየተበረታታች መሆኗንና በጠቅላላው ከአፍሪካ ሃገሮች ጋርም የምትሠራበትን አሕጉር አቀፍ ፖሊሲ በቅርቡ ይፋ እንደምታደርግ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ አስታወቁ።

አምባሳደር ናዥ በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ፣ በኤርትራና በኬንያ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ሲዘጋጁ ትናንት ከናይሮቢ በስልክ ባደረጉት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው የጉብኝታቸውን ማጠቃለያ የሰጡት።

አምባሳደር ናዥ ወደ አፍሪካ ያደረጉት ሁለተኛ ጉዟቸው ነው ዩናይትድ ስቴትስ ለዚህ የአህጉሪረቱን ጉዳዮችና ግንኙቶቿን ለምትከታተለበተ ቢሮዋ ኃላፊነት ከተሾሙት ጊዜ አንስቶ።

“ኢትዮጵያ በውጭው እንዲሁም ‘አንዳንድ’ - ባሏቸው - የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ስለከፈተችው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እያራመዱት ስላሉት መንገድ ምሥጋና ይግባውና...” ሲሉ ነው አምባሳደሩ የመክፈቻ መግለጫቸውን የጀመሩት።

በተለይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን ለየት አድርገው አንስተው ያሳደረባቸውን ስሜት ገልፀዋል።”በተመለከትኳቸው አዎንታዊ ለውጦች በእጅጉ ተበረታትቻለሁ፤ በተለይ ይህንን ሥራዬን ከጀመርኩ አንስቶ ከኤርትራ መሪዎች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ ተገናኝቼ ወደፊት ስለምናደርጋቸው እጅግ የተሻሉ ግንኙነቶች ተመካክረናል” ብለዋል።

አምባሳደር ቲቦር ናዥ በተለይ ኤርትራ በብርቱ ትወቀስበታለች የሚባለውን የሰብዓዊ መብቶች አያያዟን ከመሪዎቿ ጋር አንስተው እንደሆነ ተቀይቀው ስፋት ባላቸው የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነቶች ላይ መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቲቦር ናዥ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዞ ማጠቃለያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG