ወ/ሮ አማረች ገላኖ በደቡብ ኦሞ ዞን በመንግሥት ታጣቂ ጥይት ተደብድበው እንደሞቱ፣ የ፲፪ ዓመት ሴት ልጃቸውና ሌላው ወንድ ልጅ ደግሞ በመቁሰል አደጋ በአሁኑ ወቅት በሕክምና ላይ መሆናቸውን ባለፈው ግንቦት ፳፮ ቀን አንድ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
ዛሬ ወደዚያ ጉዳይ የገባንው የሴትዬዋ አሟሟትም ሆነ የፖለቲካ አቋም አጠያያቂ መሆኑን የሚጠቁም ደብዳቤ ከዚያው አካባቢ በመገኘቱ ነው።
አዲሱ አበበ የያዘውን ዝርዝር ያዳምጡ።