በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ “አስተማማኝ ደረጃ ላይ ነው”


ባህር ዳር ከተማ
ባህር ዳር ከተማ

የአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ “አስተማማኝ ደረጃ ላይ ነው” ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በተለይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሉም “ከመቼውም ጊዜ በላይ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት እየጠበቀ ነው” ብለዋል።

የአማራን ሕዝብ መብትና ጥቅም እናስጠብቃለን ብለው ብረት ይዘው ጫካ ገብተው የነበሩ አሥራ አራት ወጣቶች ተይዘው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጠቆሙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር “ዓላማችን መቅጣት ባለመሆኑ ትምህርት ተሰጥቷቸው ይለቀቃሉ” ብለዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ “አስተማማኝ ደረጃ ላይ ነው”
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG