በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት ከለውጥ ኃይሎች ጋር መሥራት አማራጭ የለውም አለ


የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)
የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)

"ባለፈው ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ ካየነው ሂደት አንፃር ሲታይ: ይቅርታን መሰረት ያደረገው የሕዝቡን በደል የተረዱት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የጀመሩት የለውጥ እርምጃ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ተስፋ ያጫረ ነው::" ዶ/ር አፈወርቅ ተሾመ የመዐሕድ ሊቀ መንበር::

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) - ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የ"ይቅርታ፣ የምክክር እና የሽግግር ሰላማዊ ጥሪ" የሚደግፍ መሆኑን ሰሞኑን በጽሁፍ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የድርጅቱ መግለጫ አክሎም በዐማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የቀረበውን ጥሪም "መዐሕድ ሙሉ በሙሉ በመቀበል ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ታላቅ ኃይል ለሆነው" ሲል ለአማራ ሕዝብ የህልውና እና የማንነት ጥያቄዎች ሰላማዊ መፍትሔ ያገኙ ዘንድ ከለውጥ ኃይሎች ጋር በመነጋገር ለመስራት ወስኛለሁ" ብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት ከለውጥ ኃይሎች ጋር መሥራት አማራጭ የለውም አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG