በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የተሳካ የመህር እንቅስቃሴ ለማካሄድ የሚያስችል በቂ የዘር አቅርቦት መኖሩን የእርሻና የተፈጥሮ ሚኒስቴር አስታወቀ


የክረምቱን ዝናብ በመጠቀም የተሳካ የመህር እንቅስቃሴ ለማካሄድ የሚያስችል በቂ የዘር አቅርቦት መኖሩን የእርሻና የተፈጥሮ ሚኒስትር አስታወቁ።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳብራሩት መንግሥት ለዘር ግዢ የሚሆን ከፍተኛ በጀት መድቧል። አንዳንድ ተቋማት ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ በዘር አቅርቦት እጥረት ምክንያት በሃገሪቱ ያለው የምግብ አቅርቦት ሊራዘም እንደሚችል መጠቆማቸው ይታወሳል።

አቶ አለማየሁ ብርሃኑ
አቶ አለማየሁ ብርሃኑ

የሁሉንም ቤት የሚያንኳኳ የኢትዮጵያዊያን ቀጣይ ዓመት የሚወስን ዋነኛ የምርት ወቅት ነው ክረምት። እንሆ ዝናቡም ቀጥሏል፡ የምርት እንቅስቃሴም ተጀምሯል። በድርቅ ምክንያት ካጋጠማት የምግብ እጥረት እንድታገግም የምትጠበቀው አገር ግን ሌላ ፈተና ልትጋፈጥ እንደምትችል የአንዳንድ ተቋማት ሥጋት ነው። ዝናቡ ቢጀምርም የሚዘራ ነገር ላይኖር ይችላል ባይ ናቸው። የአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት እንደሚለው 1.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን አራሽ ቤተሰቦች ለዚህ ክረምት የሚሆን በቂ አቅርቦት የላቸው። የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የተባለው ተቋምም ይሄኑን አሳብ አንጸባርቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG