በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይስስ ጽንፈኞችን ለመሳብ እየሞከረ ነው ይላሉ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ


አይስስ ጽንፈኞችን ለመሳብ እየሞከረ ነው ይላሉ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አይስስ ጽንፈኞችን ለመሳብ እየሞከረ ነው ይላሉ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ

ዋና መሰረቱ ሶሪያ የሆነው ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ዋና እንቅስቃሴውን ወደኣፍሪካ ኣህጉር በማስፋት ከናይጄሪያ ኣንስቶ ሶማሊያ ድረስ እስልምና ኣክራሪዎችን ለመሳብ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ኣንድ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ ለቪኦኤ ገለጡ ።

የእስልምና መንግስት በሊቢያዋ ሲርቲ ከተማ ባለፈው የካቲት ወር የነበሩት ተዋጊዎች ቁጥር ሁለት መቶ ብቻ እንደነበር ያስታወሱት -የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ምክትል አዛዥ ረዳት አድሚራል ማይክል ፍራንከን ዛሬ ግን በከተማዋ እና ዙሪያዋን ተዋጊዎቹ ወደሁለት ሺህ የሚጠጋ መሆኑን ኣመልክተዋል።

በብሩኪንግስ ተቁዋም የመከላከያ ፖሊሲ ኤክስፐርት ማይክል ኦሃንሎን የእስልምና መንግስት ቡድንን ለመዋጋት የሚቀረጽ ማናቸውም ስትራተጂ ሶሪያንና ኢራቅ ብቻ ሳይሆን ሊቢያንና የመንን የሚያካትት ጎላ ያለ ትኩረት እንደሚያሻው ግልጽ እየሆነ መጥቱዋል ብለዋል።

የኣፍሪኮሙ የወታደራዊ ኦፐሬሽኖች ምክትል አዛዡ ምክትል ኣድሚራል ፍራንከን ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ኣህጉር ይበልጡን ትኩረት የምታደርግባቸው ኣካባቢዎች የትኞቹ እንደሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ

“ኣምስት ዘርፎች ያሉት ጥረት ነው የምናደርገው። የመጀመሪያው በምስራቁ ኣቅጣጫ ሲሆን ያም ጸረ ኣል እልሸባብ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ያም በዚያች ጦርነት በበጣጠቃት ሀገር የተሻለ የወደፊት ዕጣ ለማምጣት ነው።

ሁለተኛው ሊቢያ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ያም በዚያ ዳኢሽንና ማሊና ሌሎች ኣካባቢዎች የሚያዳርሰውን የሰሜን ምዕራብ ኣፍሪካ ማግረብ ሀገሮች ኣልቃይዳ ቅርንጫፍን መውጋት ነው። ሶስተኛው ደግሞ ቦኮ ሃራም በቻድ ሃይቅ አካባቢ ሃገሮች እያደረሰ ያለውን ጥፋት ማስቆም ነው።” በማለት ኣብራርተዋል።

ቦኮ ሃራም ባለፉት ኣምስት ዓመታት በአፍሪካ ከሚንቀሳቀሱ ሽብርተኛ ቡድኖች ሁሉ የከፋውን ሁከት ያደረሰው መሆኑን አያይዘው የገለጹት የአፍሪኮሙ ሰራዊት ኣዛዥ በአህጉሪቱ ጎጂ የሆኑ የጦር መሳሪያ የሰዎችና የሱሱ አስያዥ መድሃኒቶች ህገ ወጥ ትልልፍ መሰባበርና ለአፍሪካ ችግሮች መፍትሄው ከአፍሪካዊያን ከራሳቸው እንዲፈልቅ የሚያግዝ የአቅም ግንባታ የጸጥታ አጋርነትን መገንባት ሌላው ጥረታችን ነው ብለዋል።

ባለፈው ወር ቁጥራቸው ወደ ሃያ ኣራት የሚሆን የኣልሸባብ ተዋጊዎች ኣልቃይዳን ከድተው የአይሲስ ታማኝነታቸውን ማወጃቸው ሲታወስ ቡድኑ በሶማሊያ የደቀነው ስጋት ምን ያህል የጎላ እንደሆን የተጠየቁት ፍራንከን

“ሶማሊያ ውስጥ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የሚባል ኣይደለም። ኣሁን ለነሱ ጤናማ ያልሆነ ሁኔታ ነው የሚታየው። ምክንያቱም ኣንዱ የኣልሸባብ ኣባል ተነስቶ ለዳኢሽ ታማኝነቱን ሲያውጅ ራሳቸው የአልሸባብ ኣባላት ወንድሞቹ ይነሱበትና ያሳድዱታል። ስለዚህ በዚያ ምክንያት ስጋቱ በዚያው ካለበት ውሱን ደረጃ ኣላለፈም።” ሲሉ አስገንዝበዋል።

ባለፈው ሳምንት ከዋና የኣልሸባብ መሪዎች አንዱ የነበረውን ሼክ ሁሴን አብዲ ጌዲን እና ሌሎች አራት ተከታዮቹን የቡድኑን አባላት ወደእስልምና መንግሥት እንዲገቡ ለመቀስቀስ መሞከራቸውን ተከትሎ ራሳቸው የአልሸባብ ተዋጊዎች እንደገደሉዋቸው ቪኦኤ ዘግቡዋል። ከዚያ ቀደም ብሎም ዘጠኝ የአይሲስ ታማኝ መሆኑ የተነገረው ሼክ አባሺህ አቡ ኑማንን ጨምሮ ዘጠኝ የአልሻባብ ኣባላት ሳኣኮው የምትባል ከተማ አጠገብ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል።

ካርላ ባብ (Carla Babb) ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጂት ታዪ አቅርባዋለች ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይዳምጡ።

አይስስ ጽንፈኞችን ለመሳብ እየሞከረ ነው ይላሉ የአፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

XS
SM
MD
LG