በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ሶማሊያ ለሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል 90 ሚ. ዶላር ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ
ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ

የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ለሚገኘውና አል ሻባብን በመፋለም ላይ ላለው የአገሪቱ ሰራዊት ድጋፍ ለሚሠጠው የኅብረቱ ሰላም አስከባሪ ልዑክ የሚውል 90 ሚሊዮን ዶላር ጠይቋል።

የኅብረቱ የፖለቲካ የሠላምና የጸጥታ ኮሚሽነር የሆኑት ባንኮሌ አዴኦዬ ለዜና ሰዎች እንዳሉት ገንዘቡ የማይገኝ ከሆነ ከ19ሺህ 600 በላይ የሚቆጠረው ሰላም አስከባሪ ኃይል ሶማሊያን እየደገፈ ለመቆየት ይቸገራል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አዲስ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ እንዲቋቋም ከአንድ ዓመት በፊት መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህም ከሁለት ዓመታት በኋላ የሶማሊያ ሠራዊት የአገሪቱን ጸጥታ ለመጠበቅ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን እስኪወስድ የሚሠራ ይሆናል ተብሏል፡፡

ልዑኩ ሥራዉን በሚገባ ለማከናወን የሚያስችለውን ገንዘብ የማያገኝ ከሆነ ሶማሊያን የመጠበቅ ኃላፊነትን አል ሻባብ ሊረከብ ይችላል ብለዋል ባንኮሌ።

የወቅቱ የሶማሊያ መንግሥት ከዚህ በፊት የነበሩት አስተዳደሮች ያልሞከሩትንና ለአል ሻባብ ጥቃት መልስ ከመስጠት ይልቅ ቡድኑ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቱንና ይህንንም ማበረታታት እንደሚያስፈልግ ባንኮሌ አክለው መግለጻቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

አሜሪካ ለሶማሊያ የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ በመጨመር ላይ ስትሆን፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት 61 ቶን የሚመዝን የጦር መሣሪያ ሞቃዲሹ ላይ ተራግፏል፡፡

XS
SM
MD
LG