በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ በሶማሊያ የሚቀጥለው ምርጫ ተግባራዊ ይሆናል


ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ
ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ

ሶማሊያ የሚቀጥለው ምርጫዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለመደው መንገድ እንደምታከናውን ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ትናንት አስታወቁ። ይህም አገሪቱ ለረጅም ግዜያት በተዘዋዋሪ መንገድ ስታደርግ የነበረውን የምርጫ ሂደት የሚያስቀር ይሆናል፡፡

ሶማሊያ አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ አካሄድ አትጠቀምም። በምትኩ የጎሳ ወኪሎችና የግዛት ም/ቤቶች ለአገሪቱ ፓርላማ አባላትን ይመርጣሉ፡፡ የፓርላማ አባላቱ ደግሞ ፕሬዚዳንቱን ይመርጣሉ። ሶማሊያ ላለፉት 50 ዓመታት አንድ ሰው አንድ ድምጽ የሚለውን የምርጫ አካሄድ አልተጠቀመችም።

“የእግዚያብሄር ፈቃድ ከሆነ የሚቀጥለውን ምርጫ በፖለቲካ ፓርቲ ሥርዓት መሠረት አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚለው መመሪያ እናከናውናለን” ብለዋል ፕሬዚዳንት ሃሳን ለፓርላማ ተወካዮች ባደረጉት ንግግር፡፡ “የፓርቲ መድረኮች የፖለቲካ ሃሳብ መሸጫዎች ይሆናሉ” ሲሉ አክለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

ጎሳዎች በሶማሊያ ፖለቲካ አካሄድ ላይ እንዲሁም የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤን፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ፕሬዚዳንት በመምረጥ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡

አገሪቱ የሚቀጥለው ምርጫዋን በግንቦት 2018 እንደምታካሂድ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG