በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ የሽብርተኞች እንቅስቃሴ መስፋፋት አስግቷል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስና አጋሮችዋ ፣ አሸባሪዎች ከደጋፊዎቻቸው የሚያገኙትን ድጋፍና የሚንቀሳቀሱባቸውን አካባቢዎች በመቀነስ ተጽእኖ ለማድረግ ቢጥሩም አሸባሪዎቹ ድርጅቶቹ ግን በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ላይ ይዞታቸውን እያጠናከሩ ይመሰላል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ የብሄራዊ የደህንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ጄፍ ሴልደን የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡

ከመከላከያ ሚኒስቴር ዋናው የቁጥጥር መምሪያ፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ በከፊል የወጣው አዲስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ፣ በዩናይትድ ስቴትስ መሪነት፣ በአፍሪካ የሚደረገው የጸረ ሽብርተኝነት ዘመቻው ጥረት፣ እንደገና እንዲፈተሽ መገደዱና አንዳንዱም እንቅስቃሴ እንዲገታ መደረጉ ተመልክቷል፡፡

ተጠባባቂው ኢንስፔተር ጄኔራል ሲያን ኦዳኔል፣ በሩብ ዓመቱ ሪፖርት ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳመለከቱት፣ አይኤስ ወይም አይሲስ ተብለው የሚታወቁት አልኬዳና እስላማዊ መንግሥትን የመሳሰሉትን ቡድኖች በመጥቀስ፣ “ ዓለም አቀፉ የዩናይትድ ስቴትስ ትብብር፣ በዚህ ረገድ ያሳየው እድገት ውስን ነው፡፡” ብለዋል፡፡ የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ከመግታት ይልቅ፣ የኮቪድ 19ን ወረርሽኝ እንዳይሳፋፋ ለማድረግ፣ የተሰጠው የቅድሚያ ትኩረት፣ አሸባሪዎቹ የበለጠ እንዲስፋፉ አዳዲስ እድሎችን እንደከፈቱላቸውም ተመልክቷል፡፡

ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በአፍሪካ የሽብርተኞች እንቅስቃሴ መስፋፋት አስግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:09 0:00


XS
SM
MD
LG