በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ማንም ሰው በማንኛውም ኹኔታ አካል ጉዳተኛ ሊኾን ይችላል” ዳኛቸው ቦጋለ

Dagnachew B. Wakene
Dagnachew B. Wakene

የአፍሪካ ወጣቶችን የመሪነት አቅም ለማጎልበት በሚል ሃሣብ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያስጀመሩት የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮ /ያሊ/፤ ማንዴላ - ዋሺንግተን ፌሎሺፕ መርኃግብር የሁለተኛው ዙር ስብሰባ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ እየተካሄደ ነው፡፡

የአፍሪካ ወጣቶችን የመሪነት አቅም ለማጎልበት በሚል ሃሣብ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያስጀመሩት የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጅማሮ /ያሊ/፤ ማንዴላ - ዋሺንግተን ፌሎሺፕ መርኃግብር የሁለተኛው ዙር ስብሰባ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባው የሚካሄደው በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሕዝባዊና መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሆም ከመደበኛ ዜጎች ጋር የሚደረገውን የስድስት ሣምንታት ሥልጠናና የልምድ ልውውጥ መርኃግብር ማጠቃለያን ተከትሎ ነው፡፡

የያሊ 2015ን ስብሰባ የከፈቱት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሲሆኑ ከተሣታፊዎቹ አምስት መቶ ወጣቶች ጋር በመድረክ ላይ ተወያይተዋል፤ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ሰጥተዋል፡፡

ከውይይቱ በኋላም ወጣቶቹ በቡድን ተከፋፍለው ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተነጋገሩ ይገኛሉ፡፡

በመርኃግብሩ ላይ ከኢትዮጵያ ተመርጠው አሥራ ሁለት ወጣት መሪዎችና ባለሙያዎች እየተሣተፉ ናቸው፡፡

ዳኛቸው ቦጋለ ይባላል። ከዐሥራ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች አንዱ ነው።ሥራው ከአካል ጉዳተኝነት ጋራ በተያያዘ ነው። ማንም ሰው በማንኛውም ኹኔታ አካል ጉዳተኛ ሊኾን ስለሚችል የአካል ጉዳተኛ ጥያቄ የአካል ጉዳተኛ ብቻ ሊኾን አይችልም ይላል።

ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርጓል

“ማንም ሰው በማንኛውም ኹኔታ አካል ጉዳተኛ ሊኾን ይችላል” ዳኛቸው ቦጋለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG