ዋሺንግተን ዲሲ —
ኬንያ፣ ላይቤርያና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ለምርጫ እየተዘጋጁ ባሉበት ጊዜ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ተንታኞች አፍሪካ ውስጥ ስላሉ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ቁልፍ ፈተናዎችና የምርጫ ሂደቶች ሊሻሻሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ለይተው ለማንጠር እየሞከሩ ናቸው፡፡
በቅርቡ ናይጀሪያ፣ ጋናና ቤኒን ውስጥ የተካሄዱ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎችና ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር ሂደቶች ለሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ዓርአያ ሊሆኑ እንደሚችሉና እንደሚገባም ነው ተንታኞቹ የሚናገሩት፡፡
ኬንያ ከአንድ ወር በኋላ ምርጫ ታካሂዳለች፡፡ የላይቤርያ ሕዝብ ደግሞ ከሦስት ወር በኋላ መሪዎቹን ይሰይማል፡፡ በሌላ በኩል ግን በዚህ የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ ወይም የፊታችን ታኅሣስ ውስጥ ሊደረግ ታስቦ የነበረው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ምርጫ የማካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ