የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፥ አንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍሎች በድጋፍ እና ክትትል ወደ ኮሌጅ የሚገቡበት የመመልመያ ፖሊሲ ተፈጻሚ እንዳይኾን ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ናቸው።
የመመልመያ ፖሊሲ(አፈርማቲቭ አክሽን)፥ ጥቁሮችን፣ ሴቶችንና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ፣ በአሜሪካ የሀብት ድልድል ተካፋይ ያልሆኑ ወይም አድልዎ ተደርጎባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ሲውል የነበረ ነው፡፡
በርእዮተ ዓለም መሥመር የተከፋፈሉት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ስድስት ለሦስት በሆነ ድምፅ፣ ላለፉት 45 ዓመታት በሥራ ላይ የኖረው ፖሊሲ አፈጻጸም እንዲቀየር ወስነዋል፡፡
ይህም፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚኖረው የትምህርት ዕድል እና የዘር ስብጥር ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ አስመልክቶ፣ በሜኒሶታ የከተማ ምክር ቤት የፍትሐዊነት እና የእኩል ዕድል ቢሮ ረዳት ዲሬክተር እና የሕግ ባለሞያ አቶ ዘካሪያስ ኀይሉን ጠይቀናል።
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም