በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዋሽ ፈንታሌው የመሬት መንቀጥቀጥ እና እስከ አዲስ አበባ የሚሰማው ንዝረት ቀጥሏል


የአዋሽ ፈንታሌው የመሬት መንቀጥቀጥ እና እስከ አዲስ አበባ የሚሰማው ንዝረት ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

ከአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ቀን ላይ ተሰምቷል::

የመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ ከፈንታሌ 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ ባለ ርቀት ላይ መሆኑን እና ከከርሰ ምድር አካባቢ የቅልጥ አለት ወደ መሬት እየሰረገ መምጣት ምክንያቱ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪ እና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ የዘርፉ ተመራማሪ እና መምህር ዶ/ር መሰለ ኃይሌ፣ አሁን እየተከሰተ ያለው አነስተኛ ሊባል የሚችል የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑን እና ቀስ በቀስ ኃይሉ እየወጣ መሆኑ የተሻለ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ሁኔታው ለአዲስ አበባ የጎላ ስጋት ይፈጥራል ብለው እንደማይጠብቁ የገለፁት ሁለቱ ምሁራን፣ ሆኖም ቀጣይነቱ እና መጠኑ በግልፅ ሊተነበይ እንደማይችል እና የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG