በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዋሽ ፈንታሌ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ


ባለፈው እሁድ መስከረም 26/2017 ዓ.ም በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በአፋር ክልል በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ
ባለፈው እሁድ መስከረም 26/2017 ዓ.ም በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በአፋር ክልል በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ

በአፋር ክልል፣ገቢ ረሱ ዞን፣አዋሽ ፈንቲዓሌ ወረዳ ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስታውቋል ።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ//ር ኤሊያስ ሌዊ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያ ኢቢሲ እንደገለፁት ማለዳ 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ ሆኖ ተመዝግቧል ።

መንቀጥቀጡ የተከሰተውም በመሬት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ባለ ቅልጥ አለት ምክንያት መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል ።

በአፋር ክልል የተከሰቱ አነስተኛ መጠን ያላቸውን የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች በተከታታይ ሲመዘግቡ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል ።

ባለፈው እሁድ፣ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ፣ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ አንዳንድ ጉዳቶች ማድረሱን የሰመራ ዩኒቨርስቲ ማስታወቁ ይታወሳል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን የከተማዋ ነዋሪዎችና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዕለቱ አስታውቀው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG