በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን - ለአዲስ አበባ ሰዎች


በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን - ለአዲስ አበባ ሰዎች
በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን - ለአዲስ አበባ ሰዎች

የተጀመረውን ለውጥ ለመደገፍ ዴሞክራሲን ለማበረታት በሚል በነገው ዕለት የተጠራው ሰልፍ በሰላም እንዲጠናነቅ “ይድረስ ለአዲስ አበቤዎች” የሚሉ መልዕክቶች እየተጻፉ ነው። መልዕክቶቹ ከግጭት እራቁ በሰላም ወጥታችሁ በሰላም ግቡ የሚል ይዘትም ያላቸው ናቸው።

በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን - ለአዲስ አበባ ሰዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:53 0:00

በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት የተጠራው ሰልፍ ዓላማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከተመረጡ ሦስት ወራት ሳይሞላቸው ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ለማሸጋገር የጀመሩት ጥረት እንዳይቀለበስ ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል ዓላማን ያዘለ እንደሆነ አዘጋጆቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በደቡብ ክልል የተፈጠሩ ግጭቶች ያሰጓቸው የመብት ተከራካሪዎችና አራማጆች ደግሞ - ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር ሰላም እንዲወርድ የተፈጠረው ተስፋም እንዳይደበዝዝ ወጣቶች ከግጭቶች ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ መክረዋል።

የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የአሁኑ ዋዜማ ራዲዮ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ይድረስ ለአዲሳባ፣ ከአዲስ አበባዊ በሚል ዛሬ በጻፈው ጹሑፍ፤ “…ሰልፉ፣ አንዷን ልጅችሽን አስደስቶ ሌላኛዋን የሚያስከፋ እንዳይሆን የሚሰጉ ድምጾች ሰማሁ። ስጋታቸው እንድሚያሰጋሽ አውቃለሁ። ልጆችሽ እንዲህ ያለውን ነገር እንዲጸየፉት አስታውሻቸው። ንገሪያቸው፤ ዘክሪያቸው፤ ገስጻቸው። ያንቺ ልጅነት፣ በአጥንትና በደም ቆጠራ፣ በመወለድ፣አለዚያም በቋንቋ ጥራት፣ ካልሆነም በሃብት ብዛት የሚገኝ ወይም የሚታጣ እንዳልሆነ አስታውሻቸው። እጅግ ያዘነ፣ የተቆጣ፣ የተቀየመ ወይም የተደሰት ሰው መልካሙን ቀን መርሳት ልማዱ ነውና፣ ደጋግመሽ አስታውሻቸው። ተማጸኛቸው። ይሰሙሻል። ማንም አይከፋ በያቸው።” ይላል።

ጹሑፉ መስፍን ነጋሽ ባለፈው ሳምንት የተፈጠሩት ግጭቶችን የሚያመላክቱ ምስሎች ማየቱና በሰልፉ ላይም አንዱ አንዱን በማስከፋት ፀብ እንዳይፈጠር በመለመን ጭምር የተፃፈ እንደሆነ ይናገራል።

ላለፉት ዐስራ ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች በመጻፍ የሚታወቁትና በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የሕግ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም እኔ አዲስ አበባ ሰልፉ ላይ ተገኝቼ ሐሳቤን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረብ ስለማልችል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መልዕክቴን አድርሱልኝ ሲሉ ጽፈዋል። ስለ ደብዳቤያቸው ተጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና ጃዋር መሐመድ፤ ሰልፉ የተዘጋጀበትን ዓላማ ለማሳካት ፍፁም ሰላማዊና በመከባበር ላይ የተገነባ ሊሆን ይገባዋል ይላል።

የቀድሞው የሕወሓት ታጋይ ዶ/ር አረጋዊ በርሄም ያለጠመንጃ በውውይት ብቻ የተከፈተው የዴሞክራሲ በር እንዳይዘጋ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ብለዋል።

(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG