በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶክትሬት ዲግሪዋን ለማጠናቀቅ ጥቂት የቀራት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተማጽኖዋን ታሰማለች


የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዋ ድርቧ ደበበ
የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዋ ድርቧ ደበበ

ትምሕርቴን ለመጨረስ 50 ሺሕ ብር ያስፈልገኛል ትላለች - አንድ ላፕቶፕና የድምጽ መቅጃ ሪከርደር ባገኝ ጥናታዊ ጹሑፌን ማጠናቀቅ እችላለሁ ብላናለች

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ሴት ተማሪዎች የመማር ዕድል አግኝተው ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ጥቃቅን ችግሮች ይዳረጋሉ። ከእነዚህ ወጣት ሴቶች መካከል ድርቧ ደበበ አንዷ ነች።

ድርቧ በመምሕራን ኮሌጅ በዲፕሎማ መርሃ ግብር በማታው የትምህርት ክፍል ትምሕርቷን ጀምራ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ ናት።

ትምሕርቷን ለማጠናቀቅ ሁለት ሴሚስተር ብቻ ይቀራታል። ነገር ግን ከጽሕፈት መሳሪያ ጀመሮ እስከ ትምህርት ቤት መመዝገቢያ የሚያስፈልጋትን ጥቂት ገንዘብ ማግኘት እንዳቃታት ትናገራለች።

ድርቧ ደበበ
ድርቧ ደበበ

ድርቧ እዚህ ለመድረስ ከመምሕራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተነስታ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች። መጀመሪያ በዲፕሎማ ከዛም ጥቂት ጊዜ ሠርታ ባጠራቀመችው ገንዘብ ተምራ ሁለተኛ ዲግሪዋን አግኝታለች። ማስተርሷን ለመማርም ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች። ከጥልፍ ሥራ ጀምሮ ልጆች እያስጠናች እንዲሁም በየመካከሉ ገጠር ትምሕርት ቤቶች እየሄደች የተጓዘችበትን መንገድ ስትተርካቸው የጥንካሬዋ ምሳሌዎች ናቸው። ድርቧ አሁን ግን እክል ገጥሟታል አምስተኛ ዓመት የፒኤችዲ ትምሕርቷን ለማጠናቀቅ የሚረዳትን ጥናት ለመስራት ወደ መስክ መውጣት ይኖርባታል። እንደነገረችን ታስተምርበት የነበረው ትምሕርት ቤት የምትማረው የቀን በመሆኑ ከሥራ አሰናብተዋታል። እንዳታስጠና ደግሞ ለመስክ መውጣት አለባት። የሁለት ሴሚስተርም ክፍያ አለባት። እዚህ ደርሳ የገጠማት እክል አስጨንቋታል።

ጽዮን ግርማ ድርቧን አነጋግራ ተከታትይን ዘግባለች።

የዶክትሬት ዲግሪዋን ለማጠናቀቅ ጥቂት የቀራት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተማጽኖዋን ታሰማለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:54 0:00

XS
SM
MD
LG