አዲስ አበባ —
የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያልውን ፋይዳ በማቀደም የበኩላቸውን ሚና በማስቀደም በህይወት ታሪካቸው ተመልክቷል፡፡
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በኢትዮጵያ ብዙ ጫና እና ተግዳሮት በማለፍ ከፍተኛ ሚና መጫዎታቸውን ነው የተጠቀሰው፡፡
አባቴ በአንድነት በመሻሻልና አብሮ በመስራት የሚያምን ፍፁም ኢትዮጵያዊ ነበር ያለው ልጃቸው ማዕሾ ሰዓረ "እሱ ስለሞተ ሀገር ይፈርሳል ማለት አይደለም" ሲል ተናግሯል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተገኝተዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ