በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካዲሳባ ጂቡቲ - ባሥር ሰዓት


በይፋ የጀመረው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መሥመር
በይፋ የጀመረው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መሥመር

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ ተመርቆ የሙከራ አገልግሎት መስጠት በይፋ የጀመረው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መሥመር ከጂቡቲ አዲስ አበባ ለመድረስ ይወስድ የነበረውን ጊዜ ወደ አሥር ሰዓት ማውረዱ ተገልጿል፡

አዲስ አበባ ላይ ዛሬ ተመርቆ የሙከራ አገልግሎት መስጠት በይፋ የጀመረው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መሥመር ከጂቡቲ አዲስ አበባ ለመድረስ ይወስድ የነበረውን ጊዜ ወደ አሥር ሰዓት ማውረዱ ተገልጿል፡፡

3.5 ቢሊዮን ዶላር /በዛሬ ምንዛሪ ከተሠላ የሰባ ሰባት ቢሊየን በላይ ብር የወጣበት የኢትዮ-ጂቡቲ ፕሮጀክት ከ750 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ነው፡፡

የባቡር መሥመሩ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሣቀስ ሲሆን ኢትዮጵያን ወደ ባለመካከለኛ ገቢ ሃገርነት ለማሸጋገር ለተያዘው የመግሥታቸው ዕቅድ መሳካት ሰፊ ድርሻ እንዳለው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አመልክተዋል፡፡

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኢል ኦማር ጌሌ ለቻይናው ሲሲቲቪ በሰጡት ቃል ፕሮጀክቱ ለአፍሪካ-ቻይና ትብብር የማዕዘን ደንጊያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከመቶ ዓመት በፊት በፈረንሣይ በተዘረጋው ኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መሥመር ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ለመድረስ በርካታ ቀናት ይወስድ የነበረ ሲሆን ጉዞውን ወደ አሥር ሰዓት ያሳጠረው አዲሱ የባቡር መሥመር የኢትዮጵያን ወጭና ገቢ ሸቀጦች በማመላለስ ከፍተኛ ትርጉም እንደሚኖረው ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የቻይና ብሄራዊ ልማትና የለውጥ ኮሚሽን ሊቀመንበር ቹ ሻኦሺ የመሥመሩን መጭ ትርጉም ሲናገሩ “መሠረተ-ልማትንና የትብብራችንን አድማስ በማስፋት ይህንን ታላቅ የማመላለሻ መሥመር ቁልፍ ወደ ሆነ የምጣኔ ኃብት ቦይነት ለማሸጋገር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተመካከርን ነን” ብለዋል፡፡

አዲሱ የባቡር መሥመር ለመጭዎቹ ስድስት ወራት በቻይናዊያን ሥራ አመራር የሙከራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ካዲሳባ ጂቡቲ - ባሥር ሰዓት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

XS
SM
MD
LG