በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትራምፕና ባይደን ርክክብ ሲጠበቅ ወረርሽኙ እየከፋ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ ጆ ባይደን

በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የ2020 ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ አገሪቱን ፈጥኖ ለመርዳት እንዲችሉ፣ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የርክክቡን ሂደት በዚህ ሳምንት እንዲጀምሩ እየጠየቁ መሆናቸውን የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሼል ኩዪን ዘግባለች፡፡

የትኛውንም የዩናይትድ ስቴትስ አካባቢ ብንመለከት፣ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን እንረዳለን፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጠያቂ የሆነው ቫይረስ ግን፣ በፖለቲካው ድራማ ተሸፍኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በ2020 ምርጫ አሸናፊ ከሆኑትና እኤአ በመጭው ጥር 20 ፕሬዚዳንት ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት፣ ከጆ ባይደን አስተዳደር የርርክብ ቡድን ጋር ሆነው፣ ለሽግግሩ ይተባበራሉ ወይስ ምን ያደርጋሉ? የሚለው ነው፡፡ እስካሁን እንደሚታየው፣ ትራምፕ ያለምንም ማስረጃ፣ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል፣ በስፋት የሚያሰራጩትን ዘመቻ የቀጠሉበት ሲሆን፣ አዲሱ አስተዳደር፣ የርርክቡንና ሽግግሩንም ሥራ እንዲጀምር አልፈቀዱም፡፡ የባይደን ቡድን አባላት፣ ወረርሽኙ በተስፋፋበት በዚህ ወቅት፣ ይህ መደረጉ አገሪቱን አደጋ ላይ ይጥላታል በማለት ይናገራሉ፡፡ የባይደን ቡድን፣ የኮቪድ 19 አማካሪ ቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር አቱል ጋዋንዴ እንዲህ ይላሉ

“ለአገሪቱ ሲባል የኮሮናቫይረሰን አስመልከቶ እየተደረገ ያለው መከላከል ምን ላይ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ የርክክብ ቡድኑ፣ ስለ ክትባቱ ስርጭት እና እቅድ፣ እንዲሁም መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ፣ የእጅ ጓንቶች፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች ክምችቶች ምን ያህል እንደሆኑ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ መተላለፍ የሚኖርባቸው መረጃዎች በርካታ ናቸው፡፡ እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ የሚጠበቁ ነገሮች ግን አይደሉም፡፡”

ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላለፉት አምስት ወራት፣ በተደረጉት የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ስብሰባ፣ አንዱንም አልተካፈሉም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት፣ የኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችለው ክትባት፣ ሥራ ላይ ስለሚውልበት የጊዜ ሰሌዳ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፡፡

“ይህ ሂደት ወዲያው ነው የሚጀምረው፡፡ በቅርቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክትባቶች ለመሰራጨት ዝግጁ ናቸው፡፡ የመጨረሻውን ይሁንታ እየተጠባበቁ ነው፡፡”

አድሚራል ብሬት ጊርዋር፣ የዋይት ሐውስ የኮሮናቫይረስ ግብረሃይል አባል ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የትራምፕ አስተዳደር የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የሚያደርገው ጥረት፣ ራሳቸው የባይደን ቡድን አባላትን ጨምሮ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፡፡ እንዲህ ይላሉ ብሬት

“በተቻለኝ መጠን ከሁሉም ጋር ግልጽ ለመሆን እፈልጋለሁ፡፡ ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህ የህዝብን ጤንነት የሚመለከትና የበርካታ አሜሪካውያንን ህይወት ማዳን ነው፡፡ ከዚህ በላይ አስፈላጊ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም፡፡”

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የቀድሞ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ጆን ቦልተን፣ የዋይት ሐውስ ሰዎች፣ ቫይረሱን አስመልከቶ ያላቸውን መረጃ፣ ለመጭው የጆ ባይደን አስተዳደር እንዲያጋሩ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል

“ርክክቡን ለምን እንደሚያስፈልግ ሪፐብሊካኑ በግልጽ ማብራራት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ በቻልነው ፍጥነት ይህንን ነገር ማከናወን ይኖርብናል፡፡” ብለዋል ጆን ቦልተን፡፡

የጆን ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ በአሁኑ ወቀት፣ በዩናትድ ስቴትስ ወደ 11 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ወደ 246ሺ የሚጠጉት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በቫይረሱ ስርጭት፣ ዩናትድ ስቴትስ በዓለም የቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘች መሆኑም ተዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የትራምፕና ባይደን ርክክብ ሲጠበቅ ወረርሽኙ እየከፋ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00


XS
SM
MD
LG