በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚዎች እርቅና ትብብር ለአዲስቷ ሱዳን


FILE - Sudan's transitional authorities and a rebel alliance sign a peace deal initialed in August that aims to put an end to the country's decades-long civil wars, in a televised ceremony in Juba, South Sudan, Oct. 3, 2020.
FILE - Sudan's transitional authorities and a rebel alliance sign a peace deal initialed in August that aims to put an end to the country's decades-long civil wars, in a televised ceremony in Juba, South Sudan, Oct. 3, 2020.

በዚህ ሳምንት፣ ወደ ካርቱም የተመለሱ አንዳንድ የሱዳን አማጽያን መሪዎች፣ ከመንግስት ጋር ያደረጉትን አዲሱን የእርቅ ስምምነት በጥሩ መንፈሰ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በርካታ የተቃዋሚና አማጽያን ኃያላትም ወደ ካርቱም ተመልሰው ሠራዊቶቻቸውን ከሱዳን መንግስት ጦር ሳይቀር በመቀላቀል አንድ የተባበረ የሱዳን ሰራዊት ለማቋቋም ጭምር መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ ልዩነትና መድልዎን አስወግደው የዜጎች እኩልነት የተረጋጠባትን አዲሲቷን ሱዳን በጋራ ለመመስረት የጋራ መንግሥት ለማቋቋም መነሳሳታቸውንም እየገለጹ መሆኑን ከካርቱም የተላከውን የማይክ አቲን ዘገባ ያስረዳል፡፡

ስምምነቱን ከመንግስት ጋር የተፈራረሙትና፣ የአማጽያኑ ድርጅቶች ጥላ ድርጅት የሆነው፣ የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት፣ አሊ ሐዲ እድሪስ፣ ባለፈው ማክሰኞ ካርቱም ውስጥ፣ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “አጋጣሚው አዲሲቱን ሱዳን ለመገንባት ወርቃማ እድል እንደሆነና፣ ሁሉም የሱዳን ዜጎች፣ በእኩል ዓይን የሚታዩበት አድርገው እንደሚመለከቱት ተናገረዋል፡፡

እድሪስ ጨምረው እንደተናገሩት፣ የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችም፣ በዚህ ሳምንት ወደ ካርቱም በመመለስ “ልባቸውን በቅንነት ክፍት ያደርጋሉ” ብለዋል፡፡ አስክተለውም፡

“ይህ ስምምነት ቀደም ብለው ከነበሩ ስምምነቶች ሁሉ የተለየና ታላቅ ስምምነት ነው፡፡ ይህ ስምምነት በሁሉም የፖለቲካ አግባቦች የተፈረመ ነው፣ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው ስለሆነ፣ መላው የሱዳን ዜጎች፣ ከስምምነቱ ጎን በመሰለፍ አዲሱን ስምምነት በጋራ ተግባራዊ እንደምናደርገው እተመማናለሁ፡፡” በማለት ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

እድሪስ እንደሚሉት፣ በደቡብ ሱዳን ጁባ በተደረገው ስምምነት መሠረት፣ “አሁን ሁሉም የተቃዋሚ ድርጅቶች የሽግግሩ መንግስት አካል ናቸው፡፡ ለጋዜጠኞች ሲናገሩም እንዲህ ብለዋል፣

“ከዛሬ ጀምሮ፣ የሽግግር መንግሥት የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎችና ፖሊሲዎች፣ ለሚያስከትሏቸው ነገሮች በሙሉ ሁላችንም ኃላፊነቱን እንወስዳለን፡፡ ሱዳናውያን ዜጎቻችን በብርቱ እንደተቸገሩ እናምናለን፡፡ አሁን የተከማቸ ነዳጅ ዳቦ እና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች አሉ፡፡ ዜጎቻችን ከዚህ አሁን ካለንበት የተሻለ ህይወት ይገባቸዋል፡፡”

ባለፈው ሳምንት፣ የሱዳንን የልዕልና ካውንስል የሚመሩት፣ ጀኔራል አቡድል ፋታ ላቡረሃን፣ በሰሩት የሰብአዊነት እና፣ በጦር ወንጀለኝነት፣ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት፣ ከሚፈለጉ ግለሰቦች በስተቀር፣ በመንግስት ላይ ጠመንጃ ላነሱ አማጽያንና ተቃዋሚዎች በሙሉ፣ ምህረት ሰጥተዋል፡፡

ባለፈው እሁድ፣ የሰላም ስምምነቱ በተከበረበት ወቅት፣ ወደ ካርቱም የተመለሱት የተቃዋሚ ቡድኖች፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት፣ መልካም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በዐሉም ላይ የተገኙት፣ በሰሜን ያለውን፣ የሱዳን ህዝብ ነጻነት ንቃናቄን የሚመሩት፣ ማሊክ አጋር ሲናገሩ “የሰላም ስምምነቱ፣ በቅን ልቦና ከተደረሰ፣ በመላው ሱዳን፣ ሰላም የሚሰፍንበትን ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል፡፡” ብለዋል፡፡ አጋር አክለውም፣ “ሁሉም የሱዳን ፖለቲካ ኃይሎች፣ በተወገዱት የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽር ዘመን፣ ለአስርት ዓመታት የወደመው የሱዳንን ማህበራዊ እሴት መልሶ ለመገንባት፣ ሰላምን እንደ መሣሪያ እንዲጠቀሙ” አሳሰባዋል፡፡

“እጆቻችንን አብዮታዊ የፖለቲካ ኃላይት ውስጥ ካሉ ወንድሞቻችን እጆች ጋር ለማያያዝ እየመጣን ነው፡፡ ስለዚህ አዲሲቷን ሱዳንን ያለምንም አድልኦ ፣ በእኩል ዜግነት እንገነባታለን፡፡ አብረን ተባብረን ከሠራን ይህ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ እኔና ሌሎች ተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች፣ ከአሁን በኋላ ሱዳን፣ ሌላ መለያየትን የምታይ አገር አለመሆኗን ማሳየት እንፈልጋለን፡፡”

አጋር ጨምረው እንደተናገሩት፣ በፊርማ የተረጋገጠው ስምምነት፣ ሁሉንም የመንግሥትና የተቃዋሚ ኃይላትን ሠራዊት፣ ወደ አንድ የሱዳን ሠራዊት ለመቀየር፣ መወሰኑ የሱዳንን ህዝብ ህብረ ልዩነት አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ኃይላት እንደ አንድ የተባበረ የሱዳን ጦር በመሆን ከተለያየውን ማህበርሰብ አካል የሆነውን የሱዳን ህዝብ ይወክላሉ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም እነዚህ ሁሉ ኃይላት አንድ ወጥ ከሆነው ሱዳን ሠራዊ ጋር ይዋሃዳሉ፡፡

የተባበረው የሱዳን ጦር፣ መች እንደሚመሰረት ግልጽ አልተደረገም፡፡ ጄኔራል አል ቡርሃን እንደተናገሩት ከሆነ፣ የሱዳን ልዕልና ምክር ቤት አባል። የሚሆኑ ሶስት ተጨማሪ አባላትን በቅርቡ ይሰይማሉ፡፡ ይህም፣ የምክር ቤቱን አባል ቁጥር ወደ 14 ከፍ ያደርገዋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት፣ ሌሎችም ለውጦች፣ በሱዳን ካቢኔዎች ውስጥ እንደሚደረጉ ተነግሯል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የተቃዋሚዎች እርቅና ትብብር ለአዲስቷ ሱዳን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00


XS
SM
MD
LG