በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ኢትዮጵያ የድንበር ግጭቱን እያባባሰች ነው በማለት ከሰሰች


ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚያወዛግባቸው የድንበር አካባቢ የሚታየው ውጥረት፣ በዚህ ሳምንትም ተባብሶ ቀጥላሏ፡፡ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ የአየር ክልሌን ጥሳ የጦር አውሮፕላኖችን እያበረረች ነው በማለትም ኢትዮጵያን ከሳለች፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ የጦር አውሮፕላኖች፣ የሱዳንን አየር ክልል ጥሰዋል በማለት ከሷል፡፡ ጥሰቱ የተፈጸመው በአወዛጋቢው አልፋሻጋ በሚባለው የድንበር አካባቢ መሆኑን ጠቅሶ “ይህ አደገኛ የሆነ ጸብ አጫሪነት ነው” ብሏል፡፡

“በኢትዮጵያ መንግሥት የሚደግፉ ታጣቂ ወንበዴዎች ቢያንስ 8 የሆኑ ሰላማዊ ዜጎችን ዋድ አሩድ እና አል ሊያ በተባሉ መንደሮች አካባቢ መግደላቸውን ድንበሩን አካባቢ ለሚጎበኙ የሱዳን ወታደሮች ተናግረዋል፡፡” ብሏል የምኒስቴሩ መግልጫ፡፡

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር፣ አብድል ፈታ አል ቡርሃን፣ በድንበር አካባቢ እየተካሄደ ስላለው ሁኔታ፣ እንዲህ ብለዋል

“ሱዳን ይህን የመሬት ጉዳይ ለረጀም ጊዜ በትዕግስት ስትከታተለው ቆይታለች፡፡ ለ25 ዓመታት የቀጠለ ጥቃት፣ ዛቻና ክስ ሲነዘር ኖሯል፡፡ ሁሉም ነገር ገደብ አለው፡፡ ሱዳን ይህን ግጭት አልጀመረችውም፡፡ ኢትዮጵያ ናት የጀመረችው፡፡ አሁን ዓይን ላጠፋ አይኑን እንደማለት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የሱዳን ሴቶችና ገበሬዎችን ገድለዋል፡፡ የእርሻ መሬቶችንም አቃጥለዋል፡፡ ይህ የሱዳን መሬት አይደለም ብለው ሱዳኖችን ወደ ገዛ መሬታቸው ገብተዋል ብለው ይከሳሉ፡፡”

የሱዳን ባለሥልጣናት እንደሚሉት፣ አል ቀዳሪፍ በተባለው የድንበር አካባቢ በሚገኙ ፣ 34 መንደሮች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡:

ሱዳንና ኢትዮጵያ፣ ለረጅም ጊዜ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውንና፣ በስሜን ምዕራብ ኢትዮጵያና የደቡብ ምስራቅ ሱዳን፣ በሚገናኙበት

“አል ፋሽካ በተባለው አካባቢ፣ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት ባለፈው ታህሳስ የጋር የድንበር ኮሚቴ መሥርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የሱዳን ወታደሮች በትግራይ ክልል የተካሄደውን የጦርነት አጋጣሚ በመጠቀም፣ አወዛጋቢዎቹን መሬቶች ወረው መያዛቸውን ይናገራሉ፡፡

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ የሱዳን ወታደሮች ከድንበሩ አካባቢ በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡና ወታደራዊ ዘመቻዎቻቸውንም እንዲያቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል አምባሳደሩ

“በጣም በቅርቡ፣ በህዳር ወር መጀመሪያ አካባቢ፣ የድንበር የጋራ ልዩ ኮሚቴው ስብሰባ ተቀምጦ ለጉዳዩ እልባት ለመሰጠት እየተነጋገር ባለበትና፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እኤአ ህዳር 4 ወደ ትግራይ በተንቀሳሰበት ሰዐት፣ ባልተለመደ ሁኔታ የሱዳን ጦር ወረራውን ሲካሂድ ተመልክተናል፡፡ የሱዳን ጦር ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ በመግባት፣ ንብረት ዘርፏል ካምፖችን አውድሟል፣ ሰዎችን አስሯል፣ አጥቅቷል፣ ገድሏል፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንንም አፈናቅሏል፡፡”

ብዙ ሱዳናውያን የአምባሳደሩን ክስ የተቃወሙ ሲሆን፣ የሱዳን ወታደሮች ዘመቻቸውን አስፋፍተው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

የደህንነት ጉዳይ ታዛቢዎች “ግጭቱ በክልሉ ላይ የሚያስተክለው ብዙ መዘዞች ይኖሩታል፡፡” ይላሉ፡፡ ባለሙያው ስዋራሚ ካሊድ እንዲህ ብለዋል

“በቅርቡ እየተባባሰ የሄደው ግጭት በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችና ወታደሮች ደህንነት ላይ በጣም አደገኛ የሆነ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ በርካታ ህዝብና ነገዶችን፣ በጦርነቱ ለማሳተፍ የሚደረገው ጥሪም አደገኛ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ በኩል ቀድሞውኑም በረሃብ እየተጠቁ ባሉ ወገኖች ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል፡”

ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት በመሸሽ፣ ምስራቃዊ ሱዳን በሚገኙ የስደተኞች ካምፓች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የሱዳን መንግሥትም ብዙዎቹን ስደተኞች ከድንበር አካባቢ ያራቃቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዘገባው የቪኦኤ ዘጋቢ ናባ ሞሄዲን ከካርቱም የላከችው ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ሱዳን ኢትዮጵያ የድንበር ግጭቱን እያባባሰች ነው በማለት ከሰሰች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00


XS
SM
MD
LG