ሀዋሳ —
በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከብቶታቸው በድረቅ እየተሞቱባቸው ለሚገኙ በኦሮምያ ክልል ለቦረና ዞን አርብቶ አደሮች ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን የዞኖቹ ባላሥልጣናት ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።
የጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ አስተዳድር ከ10 ሺህ በላይ ከብቶችን ተቀብለው ድጋፍ እያደረገ እና በግጦሽ መሬት አሰማርቶ እየተመገቡላቸው መሆኑን አስታውቋል።
በክልሉ የጋሞ ዞን ደግሞ ከ195 ሺህ በላይ ቶን መኖ ማቅረቡን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ተናግረዋል።
የቦረና ዞን ምክትል አስተዳድሪ አቶ አብዲሰላም ዋሪዮ ከ100 ሺህ በላይ ከብቶች በድርቅ መሞታቸውን ገልፀው ለተደረግው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።