ድሬዳዋ —
ቦረና ዞን ላይ በተከሰተው ድርቅ የሞቱ እንስሳት ቁጥር ከሰባ ሺህ በላይ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ የዞኑ ነዋሪዎች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ድርቁ ያስከተለውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመቀነስ ያግዛሉ ያላቸውን ሃሳቦች አቅርቧል።
ባለፈው ሳምንት ከሃምሣ ሺህ በላይ እንስሳት እንደሞቱበት ያስታወቀው ሶማሌ ክልልም የድርቁን ጉዳት ለመከላከል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።