ዌስት ባንክ ጂኒን ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትታ የተገደለችው የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አክሌ ቀብር ላይ አስከሬኗን ተሸክመው ከነበሩት አና በእስራኤል ፖሊሶች ከተደበደቡት ፍልስጣኤማውያን መካከል አንደኛውን የእስራኤል ፖሊሶች ያሰሩት መሆኑን ጠበቃው ገለጹ፡፡
አቡ ኻድር መታሰሩን የፖሊስ ቃል አቀባይ አረጋግጠው ሆኖም የታሰረው ከአርቡ የቀብር ሥነ ስርዓት ጋር በተያያዘ አይደለም ብሏል፡፡ ለምን አንደታሰረ ግን አልገለጠም፡፡
በአርቡ የሺሪን አቡ አክሌ ቀብር ላይ የአስራኤል ፖሊሶች አስከሬኗን የተሸከሙትን ሰዎች በቆመጥ ሲደበድቡ አና ባንድ ወቅት አስከሬኑ ሊወድቅባቸው ደርሶ አንደነበር የሚያሳዩት የቪዲዮ ምስሎች በዓለም ዙሪያ በስፋት መወገዙ ይታወሳል፡፡
የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ በዌስት ባንክ የአስራኤል የጦር ኃይል ወርሮት በነበረ ስፍራ በመዘገብ ላይ አንዳለች በጥይት ተመትታ መገደሏ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡