በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታዋቂዋ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አክሌህ ዌስት ባንክ ጂኒን ከተማ ውስጥ ተገደለች

ታዋቂዋ የአልጀዚራ አረብኛ ሥርጭት ጋዜጠኛ ሺሪን አቡ አክሌህ በእስራኤል በተያዘው በዌስት ባንክ ጂኒን ከተማ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ የእስራኤል ኃይሎች በወረሩት ስፍራ በመዘገብ ላይ ሳለች በጥይት ተመትታ ተገድላለች።

ጋዜጠኛዋ እና ሌላው በጥይት ተመትቶ የቆሰለው ጋዜጠኛ የተኮሱብን የእስራኤል ኃይሎች ናቸው ያሉ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ የተመቱት በፍልስጥኤማውያን በተተኮሰ ጥይት መሆኑን ማስረጃ አለኝ ስትል አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋም የሆነችው ዝነኛው ፍልስጣኤማዊት ጋዜጠኛ ሽሪን ከቆሰለች በኋላ ብዙም ሳትቆይ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ጀርርባው ላይ ተመትቶ የቆሰለው ፍልስጥኤማዊ ጋዜጠኛ አሊ ሳሙዲ ሆስፒታል ተኝቶ እየታከመ መሆኑን ተገልጿል።

መደበኛ ሥርጭቱን አቋርጦ የጋዜጠኛ ሲሪንን ሞት የተናገረው አልጀዚራ ባወጣው መግለጫ "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የእስራኤልን ወራሪ ኃይል ባለደረባችንን ሆን ብሎ ዒላማ አድርጎ በመግደሉ በተጠያቂነት መያዝ አለበት" ብሏል።

የእስራኤል የጦር ኃይል በበኩሉ ጂኒን ውስጥ ኃይሎቹ በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ ከባድ የተኩስ እና የፈንጂ ጥቃት ስለተሰነዘረባቸው በአጸፋው ተኩሰዋል ብሏል። አስከትሎም ጋዜጠኞቹ የተመቱት በፍልስጥኤማውያን በተተኮሰ ጥይት ሊሆን ስለሚችል ምርመራ እያካሂድን ነን ብሏል።

የሃምሳ አንድ ዓመቷ ሲሪን እአአ ከ1997 ጀምራ የአልጀዚራ ቴሌቭዢን ጋዜጠኛ ስትሆን ከፍልስጥኤም ግዛቶች ዙሪያ በምታስተላልፋቸው ሪፖርቶቿ ትታወቃለች።

XS
SM
MD
LG